Fana: At a Speed of Life!

ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ትምህርት ቤቶችን በመገንባት ለሰሩት ስራ የምስጋና መርሃግብር እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 2 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ትምህርት ቤቶችን በመገንባት ለሰሩት ስራ ምስጋና የሚሰጥበት መርሃ ግብር በትምህርት ሚኒስቴር አዘጋጅነት እየተካሄደ ነው።

በመርሃ ግብሩ ላይ ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ፣ፕሬዚደንት ሳህለወርቅ ዘውዴ፣ የትምህርት ሚኒስትር ዶክተር ኢንጅነር ጌታሁን መኩሪያ ፣ ሌሎች ሚኒስትሮች እና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

በስነ ስርአቱ ላይ ትምህርት ባልተዳረሰባቸው አካባቢዎች ትምህርት ቤቶችን በመገንባት ለሰሩት መልካም ስራ ለቀዳማዊት እመቤት ምስጋና ቀርቧል።

የትምህርት ሚኒስትሩ ዶክተር ኢንጅነር ጌታሁን መኩሪያ ፤ በትውልድ ግንባታ ወሳኝ ሚና ለሚጫወተውና የመልካም ፍሬ ማፍሪያ የሆኑ ትምህርት ቤቶችን በመገንባት ለሰሩት መልካም ስራ ለቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ምስጋና ይገባቸዋል ብለዋል።

የመፅሀፎቻቸውን ሽያጭ ገቢ ለትምህርት ቤቶች ግንባታ እንዲውል በመወሰናቸውም ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ምስጋና አቅርበዋል።

እስካሁን 20 የሚሆኑ ትምህርት ቤቶች በቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ተገንብተው ወደ ስራ የገቡ ሲሆን በርካታ ትምህርት ቤቶችም በግንባታ ላይ ይገኛሉ።

በሀብታሙ ተ/ስላሴ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.