Fana: At a Speed of Life!

ቀጠናውን ለማረጋጋት በተደረገው ህግን የማስከበር ስራ 1ሺህ 1 የሚሆኑ ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር በማዋል ጉዳያቸው በህግ እየታየ ነው

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 4፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ቀጠናውን ለማረጋጋት በተደረገው ህግን የማስከበር ስራ 1ሺህ 1 የሚሆኑ ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር በማዋል ጉዳያቸው በህግ እየታየ መሆኑን የመተከል ዞን ኮማንድ ፖስት አስታወቀ።
በዞኑ በተፈጠረው የሰዎች ሞት እና መፈናቀል ምክንያት የሆኑ 284 ጸረ ሰላም ሃይሎች መደምሰሳቸውን ኮማንድ ፖስቱ ገልጿል።
መንግስት የሰጣቸውን ሃላፊነት ወደ ጎን በመተው ለጸረ ሰላም ሃይሉ መረጃ በመስጠት የተጠረጠሩ ከክልል እስከ ወረዳ በሚገኙ 66 አመራሮች ላይም እርምጃ መወሰዱን ኮማንድ ፖስቱ አስታውቋል፡፡
ኮማንድ ፖስቱ እያከናወነ ባለው ኦፕሬሽን 50 ሰዎች የተማረኩ ሲሆን ÷43 የሚሆኑት ደግሞ በመግባባት እጅ ሰጥተዋል።
በተደጋጋሚ ግጭቱ እንዳይቆም ህዝባዊ ሃላፊነት ባልተወጡ 32 የፖሊስ አባላትና 35 የጸረ ሽምቅ አባላትን በቁጥጥር ስር በማዋል ጉዳዩም በህግ እየታየ ይገኛል ነው የተባለው።
ቀጠናውን ለማረጋጋት በሚደረገው ህግን የማስከበር ስራ 119 ዘመናዊ የጦር መሳሪያ ፣108 ኋላ ቀር መሳሪያ በአጠቃላይ 227 የጦር መሳሪያ እና የተለያዩ የወታደር ልብሶችም ተይዘዋል።
በቀጠናው በተፈጠረው አለመረጋጋት እስካሁን 22 ሺህ 768 የህብረተሰብ ክፍሎች ከቀያቸው የተፈናቀሉ ሲሆን ÷ለእነዚህ ወገኖች ሰብዓዊ ድጋፍ በማድረግ እና ወደ ነበሩበት ለመመለስ ርብርብ እየተደረገ እንደሆነም ተገልጿል።
በመተከል ዞን የተከሰተውን አለመረጋጋት በዘላቂነት ለመፍታት 2ሺህ 679 አዲስ የሚሻ አባላት በማሰልጠን ከህብረተሰቡ ጋር ቀጠናውን እንዲጠብቁ መደረጉን ከመተከል ዞን ኮሙዩኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል www.youtube.com/fanatelevision ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.