Fana: At a Speed of Life!

ቂርቆስ ክፍለ ከተማ 5 ሚሊየን ብር የሚያወጡ የህክምና ግብዓቶች ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ጥር 15፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ቂርቆስ ክፍለ ከተማ 5 ሚሊየን ብር የሚያወጡ ከ460 በላይ አይነት መድሀኒትና የህክምና ግብዓቶች ድጋፍ አደረገ፡፡
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ፥በአማራ ክልል በደቡብ ወሎ ዞን ለደሴ ከተማ የቧንቧ ዉሀ ጤና አጠባበቅ ጣቢያ ድጋፍ አድርጓል፡፡
በክፍለ ከተማው ድጋፍ የተደረጉ 460 አይነት የመድሃኒት እና የህክምና ግብአቶችን የክፍለ ከተማው ብልፅግና ፓርቲ ፅህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ታረቀኝ ገመቹ ፥ ለደሴ ምክትል ከንቲባና የጤና መምሪያ ሀላፊ አቶ ሰዒድ ሙባረክ ማስረከባቸውን ከክፍለከተማው የኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት ማህበራዊ ትስስር ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
በተመሳሳይም ኑሯቸውን በአሜሪካ የሆነ እና በአትላንታ የኢትዮጵያ ማህበረሰብ የቦርድ ሰብሳቢ የሆኑት ሚሚ ታደሰ፥ በሰሜን ሸዋ ዞን ጣርማበር ወረዳ ለሚገኘውና በጦርነቱ ጉዳት ለደረሰበት ሞሰቢት አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት 400 ሺህ ብር ድጋፍ አድርገዋል፡፡
የደረሰውን ውድመት በአካል በመገኘት ለመመልከት ነው የመጣነው ያሉት ወ/ሮ ሚሚ፥በአትላንታ ለሚገኘው የኢትዮጵያ ማህበረሰብ የችግሩን ስፋት በማስረዳት ድጋፍ እንዲያደርጉ አርአያ በመሆን እሰራለሁ ማለታቸውን ባልደረባችን ሳምራዊት የስጋት ዘግባለች፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.