Fana: At a Speed of Life!

ቅዱስ ጊዮርጊስና ኮረንቲያስ በጋራ ለመስራትና ልምድ ለመለዋወጥ ተስማሙ

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 21 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ቅዱስ ጊዮርጊስ እግር ኳስ ክለብና የብራዚሉ አንጋፋ ክለብ ኮረንቲያስ በጋራ ለመስራትና ልምዳቸውን ለመለዋወጥ ተስማሙ፡፡

የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ማህበር ስራ አመራር ቦርድ አባላት ከኮረንቲያስ ክለብ ተወካይ ጋር በአዲስ አበባ ምክክር አድርገዋል፡፡

ኮረንቲያስ በተጫዋቾች አሰለጣጠን፣ በክለብ አስተዳደር፣ በታዳጊዎች የስልጠና ስርዓት፣ በእግር ኳስ ፍልስፍና፣ በቢዝነስና ማርኬቲንግ እንዲሁም በደጋፊዎች አያያዝና አስተደዳር ረገድ ያለውን የካበተ ልምድ ለቅዱስ ጊዮርጊስ ለማጋራት ዝግጁ መሆኑን የክለቡ ተወካይ ፓውሎ ፓን ተናግረዋል፡፡

የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ማህበር የስራ አመራር ቦርድ ሊቀመንበር አቶ አብነት ገብረመስቀል ከብራዚሉ ኮረንቲያስ ክለብ ጋር የተጀመረው ግንኙነት የቅዱስ ጊዮርጊስን ክለብ አሰራርና አመራር ዓለም አቀፍ ደረጃ የጠበቀ ለማድረግ የተጀመረው ጥረት አካል መሆኑን ገልጸዋል፡፡

የብራዚሉ ኮረንቲያስ ክለብ በታላላቅ የንግድ ድርጅቶች ስፖንሰር የሚደረግ እንደመሆኑ ቅዱስ ጊዮርጊስ ከዚህ ክለብ ብዙ ልምዶችን እንደሚወስድም ነው የገለጹት፡፡

በሁለቱ ክለቦች መካከል በአዲስ አበባና በሳኦፖሎ የወዳጅነት ጨዋታዎች በማድረግ በእግር ኳሱ ዘርፍ የትብብር ግንኙነት የበለጠ ማጠናከር ስለሚቻልበት ጉዳይም ሃሳብ መለዋወጣቸውን ከክለቡ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.