Fana: At a Speed of Life!

ቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ክለብ የቡድኑን ዋና እና ረዳት አሰልጣኞቹን አገደ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 4፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ማህበር ሥራ አመራር ቦርድ በዋና አሰልጣኝ፣ ረዳት አሰልጣኞች እና የግብ ጠባቂ አሰልጣኝ ላይ ጊዜያዊ እገዳ መጣሉን አስታወቀ።

የስፖርት ማህበሩ ሥራ አመራር ቦርድ ባደረገው ስብሰባ የዋናውን እግር ኳስ ቡድን ወቅታዊ አቋም በሰፊው ከገመገመ በኋላ ውሳኔ ማሳለፉን አስታውቋል።

በዚህም በሶስቱ አሰልጣኞች ላይ ጊዜያዊ እገዳ በመጣል ዋናውን ቡድን በማሰልጠን ተግባር ላይ እንዳይሳተፉ ውሳኔ አሳልፏል።

እንዲሁም የቴክኒክ ኮሚቴው እንዲሰናበት ሥራ አመራር ቦርዱ ወስኗል።

በተጨማሪም የቀድሞውን የቡድን መሪ አቶ ታፈሰ በቀለ የሥራ አመራር ቦርድ አባል ወደ ሀላፊነታቸው እንዲመለሱ መወሰኑን ከክለቡ የፌስ ቡክ ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.