Fana: At a Speed of Life!

ቋሚ ኮሚቴው የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽንን የሥራ እንቅስቃሴ ጎበኘ

አዲስ አበባ ፣ታህሳስ 20 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የከተማ ልማት፣ ኮንስትራክሽን እና ትራንስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣንን የሥራ እንቅስቃሴ በስፍራው በመገኘት ጎብኝቷል፡፡
የቋሚ ኮሚቴው የቡድን አስተባባሪ አቶ ካሚል አሕመድን ጨምሮ ሌሎች አባላት በመስክ ምልከታው ላይ ተገኝተዋል፡፡
ኮሚቴው በመስክ ምልከታው የባልስልጣን መሥሪያ ቤቱን አጭር ሪፖርት በማዳመጥ የተለያዩ የሥራ ክፍሎችን ጎብኝቷል።
የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ኮሎኔል ወሰንየለህ ሁነኛው ሪፖርቱን ባቀረቡበት ወቅት÷ ብቁ የአቪየሽን ባለሙያዎችን በማፍራት ረገድ እየተሰራ ያለውን ስራ፣ ደህንነቱ የተጠበቀ የአየር ትራንስፖርት አገልግሎት እንዲኖር የተሠሩ ሥራዎችን እንዲሁም የግሉ ዘርፍ በአቪዬሽን መስክ ላይ ያለውን ተሳትፎ በተመለከተ ገለጻ አድርገው ከቋሚ ኮሚቴው ጋር ውይይት ተደርጓል፡፡
ቋሚ ኮሚቴው የምልከታውን ግብረ-መልስ በቅርቡ ይሰጣል ተብሎ እንደሚጠበቅ ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል www.youtube.com/fanatelevision ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.