Fana: At a Speed of Life!

ቋሚ ኮሚቴዎች ተቋማት ችግሮችን ለመፍታት በቅንጅት ሊሰሩ እንደሚገባ አሳሰቡ

አዲስ አበባ፣ ጥር 19፣ 2013 (ኤፍቢሲ) በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የተፈጥሮ ሀብት፣ መስኖና ኢነርጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት እና የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በቅንጅት እንዲሰሩ አሳስቧል፡፡

ቋሚ ኮሚቴው የኤሌክትሪክ ኃይል መቆራረጥና መሰል ችግሮችን ለመፍታት ተቋማቱ በቅንጅት ሊሰሩ ይገባል ብሏል በ6 ወር ግምገማው፡፡

ተቋማቱ እርስ በርስ በመነጋገር ቢሰሩ የህብረተሰቡን እርካታ ማረጋገጥ እንደሚችሉ ያነሳው፡፡

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ለክልል ቢሮዎች ግብዓት በሟሟላት አበረታች ስራ መስራቱ የተገለጸ ሲሆን አዲስ ደንበኞችን የኤሌክትሪክ ኃይል ተጠቃሚ ለማድረግ፣ የትራንስፎርመር መቃጠል፣ በሰራተኞችና በህብረተሰቡ ላይ የሚደርሱ አደጋዎችን እንዲሁም የኃይል መቆራረጥን ለመቀነስ ተገቢ እርምጃ አለመወሰዱን ነው የተጠቀሰው፡፡

በሌላ በኩል የንግድና ኢንዱስትሪ ጉዳዮቸ ቋሚ ኮሚቴ የኢትዮጵያ ምርት ገበያ ባለስልጣን እና የምርት ገበያ የግማሽ ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት በገመገመበት ወቅት ተቋማቱ ለስኬት እንዲበቁ ተቀራርበው መስራት ይጠበቅባቸዋል ብሏል፡፡

ቋሚ ኮሚቴው አዳዲስ ምርቶችን በማስተዋወቅ ወደ ገበያ እንዲገቡ መደረጉ፣ የግብይት ደንቡን በማሻሻል ላቀናባሪዎችና እሴት ለሚጨምሩ አዳዲስ ኢንዱስትሪዎች እድል መከፈቱ እንዲሁም በግማሽ ዓመቱ የምርት ገበያ ወደ 320 ሺህ ቶን ምርት ከግብይት ዋጋ አንጻር ወደ 19 ነጥብ 8 ቢሊየን ብር ዋጋ የሚያወጡ ምርቶችን በመገበያየት ትርፋማ መሆኑም በጥንካሬ ተነስቷል፡፡

በምርት ገበያ የሚነሱ ቅሬታዎች በተለይ የገበያ ጥሰቶችን እንዲሁም የመጋዘንና የመሰረተ-ልማት ግንባታዎችን ትኩረት ሰጥቶ መስራት እንደሚገባ መነሳቱን ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.