Fana: At a Speed of Life!

በሀላባ ዞን ለሕዳሴ ግድብ ግንባታ 27 ነጥብ 4 ሚሊየን ብር ድጋፍ ተደረገ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 10 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በሀላባ ዞን ለሕዳሴ ግድብ ግንባታ የ27 ነጥብ 4 ሚሊየን ብር ድጋፍ ተደረገ።

“የሕዳሴ ቱር የመኪና ላይ ቅስቀሳ” በሀላባ ቁሊቶ ተካሄዷል፡፡

የሀላባ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አማካሪ አቶ ከድር ቆርቾ ÷ የዞኑ ሕዝብ የሕዳሴ ግድብ ግንባታ ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ እስከ አሁን ድረስ የ27 ነጥብ 4 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ማድረጉን ገልጸዋል፡፡

የሕዳሴ ግድብ ግንባታ ሕዝባዊ ተሳትፎ ማስተባበሪያ ብሔራዊ ምክር ቤት ጽህፈት ቤት ተወካይ አቶ ዳንኤል ተስፋዬ በበኩላቸው÷ ለሕዳሴ ግድብ ግንባታ በሀገሪቱ እስከ አሁን ድረስ 14 ነጥብ 4 ቢሊየን ብር ተሰብስቦ የግድቡ 78 ነጥብ 3 በመቶ ግንባታ ተከናውኗል ብለዋል፡፡

በሀላባ ቁሊቶ የሕዳሴ ቱር የመኪና ላይ ቅስቀሳውን ያደረገው የሕዳሴ ግድብ ግንባታ ሕዝባዊ ተሳትፎ ማስተባበሪያ ብሔራዊ ምክር ቤት ከኢትዮጵያ ታሪክ፣ ባህልና ቅርስ አድን ድርጅት ጋር በመተባበር ነው፡፡

በቅስቀሳው ላይ የዞኑ ምክር ቤት የ10 ሺህ ብር የደረት ፒን የገዛ ሲሆን የቦንድ ሽያጭና የ8100A መርሐ ግብርም ተካሂዷል፡፡

በቀጣይም ከየካቲት 10 እስከ የካቲት 13 ቀን 2013 ዓ.ም ድረስ የሕዳሴ ቱር የመኪና ላይ ቅስቀሳው በወላይታ፣ ኮንሶ፣ ጋሞ እና ደቡብ ኦሞ ዞን ከተሞች እንደሚካሄድ ከደቡብ ክልል መንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፦ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ዩቲዩብ ቻናል፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.