Fana: At a Speed of Life!

በሀረሪ ክልል ኮሮና ቫይረስን ከመከላከልና ከመቆጣጠር አንፃር እየታዩ ያሉ መዘናጋቶች እንዲቀረፉ በትኩረት መስራት አስፈላጊ ነው-አቶ ኦርዲን በድሪ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 6 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በሀረሪ ክልል ኮሮና ቫይረስን ከመከላከልና ከመቆጣጠር አንፃር እየታዩ ያሉ መዘናጋቶች እንዲቀረፉ በትኩረት መስራት አስፈላጊ መሆኑን የሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ ተናገሩ፡፡
በሀረሪ ክልል የኮቪድ-19 ወረርሽኝን ለመከላከልና ለመቆጣጠር በቀጣዮቹ ስድስት ወራት የሚተገበር መድሀኒት ነክ ያልሆኑ የጥንቃቄ እርምጃዎች የንቅናቄ ትግበራ ማብሰሪያ መድረክ ተካሄዷል፡፡
በመድረኩም የሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ÷ በሀገሪቱ ብሎም በክልሉ የበሽታውን ስርጭት ለመከላከልና ለመቆጠጣር ህዝቡ፣ መንግስትና ፓርቲ ርብርብ በማድረግ አበረታች ውጤት ተመዝግቧል፡፡
ለዚህም የሀይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ አፎቻዎችና እድሮች ከፍተኛ አስተዋፅኦ አበርክተዋል ብለዋል፡፡
በክልሉ ቀደም ሲል የነበረው የህብረተሰቡ የማስክ አጠቃቀም መልካም የሚባል የነበረ ቢሆንም በአሁኑ ወቅት ግን መቀዛቀዝ እየተስተዋለ እንደሚገኝ ርዕሰ መስተዳድሩ ገልጸዋል።
በመሆኑም በአሁኑ ወቅትም ቀደም ሲል የተጀመሩ መልካም ተግባራትን ማስቀጠል ይገባል ነው ያሉት።
በተለይም በገበያ ስፍራዎች፣ በትራንስፖርት እና ሌሎች አካባቢዎች ላይ ማስክ በመጠቀም፣ ርቀትን በመጠበቅ፣ እጅን በመታጠብ እና ንፅህናን በመጠበቅ ቫይረሱን ከመከላከል አንፃር ያሉ ክፍተቶችን ለማረምና እየታዩ ያሉ መዘናጋቶችን እንዲቀረፉ በትኩረት መስራት አስፈላጊ ነውም ነው ያሉት።
ለዚህም የግንዛቤ ማስጨበጥ ስራዎችን ማጎልበት እና የጥንቃቄና የክልከላ መመሪያዎችን ተግባራዊ የማድረግ ስራዎች በቀጣይ ትኩረት ተሰጥቶ እንዲሰራ አሳስበዋል።
የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ወይዘሮ ሚስራ አብደላ በበኩላቸው÷ እንደተናገሩት በንቅናቄ ስራው ቀደም ሲል የነበሩ ጠንካራ ጎኖችን ማጎልበትና ክፍተቶችን በመቅረፍ አስፈላጊ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
ቫይረሱን ከመከላከልና ከመቆጣጠር አንፃር ከአመራሩ ጀምሮ እየታዩ ያሉ መዘናጋቶችን መቅረፍ አስፈላጊ መሆኑን አመላክተዋል፡፡
የንቅናቄ ስራው ውጤታማ እንዲሆንም የሚመለከታቸው አካላት በቅንጅት መስራትና ሀገርንና ህዝብን የማዳን ሃላፊነተትን መወጣት እንደሚገባ ምክትል ርዕሰ መስተዳድሯ ወይዘሮ ሚስራ አብደላ ገልፀዋል፡፡
በምክትል ርዕሰ መስተዳደር ማዕረግ የክልሉ ብልፅግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ሃላፊው አቶ አብዱጀባር መሀመድ÷ ከአመለካከት ጋር ተያይዞ እየተስተዋሉ ያሉ ክፍተቶችን ከመቅረፍ አንፃር በትኩረት መንቀሳቀስ አስፈላጊ መሆኑን ጠቁመው በተለይም በእምነት ተቋማት፣ በገበያ ስፍራዎችና በትምህርት ቤቶች ላይ ልዩ ጥንቃቄና ትኩረት መስጠት ይገባል ሲሉ ተናግረዋል፡፡
የሀረሪ ክልል ጤና ጥበቃ ቢሮ ኃላፊ አቶ ኢብሳ ኢብራሂም በክልሉ ባለፉት ወራት ስርጭቱን ከመቆጣጠርና ከመከላከል አንፃር ውጤታማ ስራዎች ተሰርተዋል ብለዋል፡፡
ሆኖም በአሁኑ ወቅት በክልሉ ህዝቡ ዘንድ የመዘናጋትና የቸልተኝነት ችግር እየተስተዋለ በመሆኑ ይህንን ችግር ለመቅረፍ ፣ ስርጭቱን ለመቆጣጠርና ለመከላከል በቀጣይ በትኩረት ይሰራል ማለታቸውን ከሀረሪ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.