Fana: At a Speed of Life!

በሀረር የበጎ አድራጎት ስራ ተከናወነ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 12፣ 2013 (ፈ ቢ ሲ) የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር በሀረሪ ክልል ለሚገኙ አቅመ ደካሞችና አረጋውያን የምግብና የአልባሳት ድጋፍ አደረገ።

በከተማና ገጠር ለሚገኙ ዘጠኙ ወረዳዎች የተለገሰውን ድጋፍ የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስትሯ ኢኒጅኒየር አይሻ መሐመድ ለክልሉ ሴቶችና ህፃናት ጉዳይ ጽሕፈት ቤት አስረክበዋል፡፡

በድጋፉ ከ8 ነጥብ 4 ሚሊየን ብር በላይ የሚያወጡ 197 የብርድ ልብስ፣ 2 ሺህ ኪሎግራም ስኳር፣ 500 ሊትር የምግብ ዘይት፣ 1 ሺህ ኪሎግራም ፓስታ፣ 430 ኪሎግራም ምስር እና የተለያዩ አልባሳት እንደሚገኙበት ነው የተገለፀው፡፡

የምግብና የአልባሳት ድጋፉንም የወረዳ አመራሮች የተረከቡ ሲሆን ለሚገባቸው የህብረተሰብ ክፍሎች እንደሚያከፋፍሉ አስታውቀዋል።

የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር ካደረገው የምግብና የአልባሳት ድጋፍ በተጨማሪ የሦስት ችግረኞችን መኖሪያ ቤት የማደስ ስራ በሚኒስትሯ ኢኒንጂነር አይሻና በሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ ተጀምሯል።

በተሾመ ኃይሉ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.