Fana: At a Speed of Life!

በሀዋሳ ከተማ ሳምንታዊ የማስ ስፖርት ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 4፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ሳምንታዊ የማስ ስፖርት ተካሄደ።
በፕሮግራሙ ላይ የሀዋሳ ከተማ ምክትል ከንቲባ ረዳት ፕ/ር ፀጋዬ ቱኬን ጨምሮ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች በሀዋሳ አርቴፊሻል ስታዲየም በመገኘት የጋራ ስፖርት ሰርተዋል።
የማስ ስፖርት ፌስቲቫሉን በይፋ ያስጀመሩት የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ም/ከንቲባ ረዳት ፕ/ር አቶ ፀጋዬ ቱኬ ስፖርት አካላዊ፣ አእምሯዊ እና መንፈሳዊ ጤንነትን በማላበስ ለራሳችን፣ለቤተሰባችን እና ለሀገራችን እድገትና ብልፅግና የበኩላችንን አስተዋፅኦ እንድንወጣ የጎላ ሚና አለው ብለዋል።
የዙሁ አካል የሆነውና በዛሬው ዕለት በይፋ የተጀመረው ይህ የማስ ስፖርት ዘውትር እሁድ በአሮጌው የሀዋሳ ስታዲየም የሚካሄድ መሆኑንም ረዳት ፕ/ር ፀጋዬ ቱኬ ገልፀዋል።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል www.youtube.com/fanatelevision ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.