Fana: At a Speed of Life!

በሀገሪቱ የተጀመረው የብልጽግና ጉዞ እውን እንዲሆን የስፖርቱ ዘርፍ የላቀ ድርሻ አለው- አቶ ርስቱ ይርዳ

አዲስ አበባ፣ ጥር 15፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ክልል ስፖርት ምክር ቤት 21ኛ መደበኛ ጉባኤ በአርባ ምንጭ ከተማ እያካሄደ ነው።
የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እና የክልሉ የስፖርት ም/ቤት ሰብሳቢ አቶ ርስቱ ይርዳ ፥ ስፖርት ለሰው ልጆች ሁለንተናዊ ስብዕና ለመገንባት ሚናው ከፍተኛ ነው ብለዋል።
ወጣቶች ያላቸውን ዝንባሌ በመጠቀም ውጤታማ እንዲሆኑ የስፖርቱን ዘርፍ ለማሳደግ በትኩረት ይሰራል ነው ያሉት።
በሀገሪቱ የተጀመረው የብልጽግና ጉዞ እውን እንዲሆን የስፖርቱ ዘርፍ የላቀ ድርሻ እንዳለውም ጠቁመዋል።
ከዚህ ቀደም የስፖርቱ ዘርፍ ትኩረት ሳያገኝ መቆየቱን የተናገሩት ርዕሰ መስተዳድሩ፥ አንድነትን ፣ መተባበርን፣ ፍቅርን ፣ በአብሮነት የበለጸገ ማህበረሰብን፣ ጤንነቱ የተጠበቀ አምራች ህብረተሰብ ለመፍጠር ትልቅ አቅም ያለው ዘርፍ መሆኑን አብራርተዋል።
በሀገር አቀፍ ደረጃ ያጋጠመን የህልውና ጫና በስፖርቱ ዘርፍ ላይ ያሳደረው ተጽዕኖ ከፍተኛ ነው ሲሉም ርዕሰ መስተዳድሩ ተናግረዋል።
ኢትዮጵያውያን አንድነታችንን አጠናክረን ጠላት ያሰበው እንዳይሳካ ድል በመንሳት፥ ኢትዮጵያ ከፍ ብላ በታየችበት ማግስት የስፖርት ምክር ቤቱን ጉባኤ ማካሔዳችን የተለየ ያደርገዋል ብለዋል።
በቀሪ ጊዜያት የሀገራችንን ህልውና የሚፈታተን ነገር እንዳይኖር የጀመርነው ህብረት እና የአይበገሬነት መንፈስ በማጎልበት በስፖርት ልማቱ ሀገራችንን ለማሳደግ የምንተጋበት ጊዜ እንደሚሆንም ተናግረዋል።
የደቡብ ክልል በሀገራችን ስፖርት ላይ ጉልህ ሚና ያለው ክልል ነው ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ፥ ለኢትዮጵያ ኩራት መሆን የሚችሉ ስፖርተኞችን ማፍራት መቻሉን ጠቁመዋል።
ሆኖም ግን ክልሉ ካለው አቅም አንጻር በዘርፉ የተመዘገበው ውጤት ዝቅተኛ ነውም ነው ያሉት።
ያሉንን እድሎች በማስፋት በየዘርፉ የሚሳተፉ ስፖርተኞችን ለማፍራት በትኩረት እንሰራለን ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ በቀጣይ ጊዜያት የሚያጋጥሙ ችግሮችን በመፈተሽ ውጤታማ ስራ መስራት ይጠበቅብናል ሲሉም አስረድተዋል።
የደቡብ ክልል ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ሀላፊ አቶ ተስፋዬ ብላቱ በበኩላቸው፥ በስፖርቱ ዘርፍ የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በትኩረት እንደሚሰራ ገልጸዋል።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.