Fana: At a Speed of Life!

በሀገር አቀፍ ደረጃ የማህጸን በር ካንሰር መከላከያ ክትባት እየተሰጠ ነው

አዲስ አበባ ፣ ጥር 19፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የማህጸን በር ካንሰር በሽታ መከላከያ ክትባት ከጥር 17 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ ከጋምቤላና ከቤኒሻንጉል ክልል በስተቀር በመላ ሃገሪቱ ዕድሜያቸው 14 ዓመት ለሆናቸው ሴት ልጃገረዶች እየተሰጠ ነው፡፡

የጤና ሚኒስቴር እንዳስታወቀው የማህጸን በር ካንሰር ክትባት በሃገራችን ከተጀመረ 3ኛ ዓመቱ ሲሆን በየዓመቱም 1 ነጥብ 2 ሚሊየን ልጃገረዶች ይከተባሉ፡፡

የዘንድሮውን ዓመት መርሃግብር ለየት የሚያደርገው በ2012 ዓ.ም ጥቅምት ወር ላይ የመጀመሪያውን ዶዝ የወሰዱ ነገር ግን 2ኛውን ዶዝ እንዲወስዱ የሚጠበቁ እና በ2013 ዓ.ም ዕድሜያቸው 14 ዓመት ለሞላቸው አዲስ ልጃገረዶች ክትባቱ ይሰጣል ብሏል፡፡

በጠቅላላው ለ2 ነጥብ 4 ሚሊየን ሴት ልጃገረዶች በያዝነው ዓመት ክትባቱን ይወስዳሉ ተብሎ ይጠበቃል ነው ያለው ሚኒስቴሩ፡፡

ክትባቱ ዕድሜያቸው 14 ዓመት ለሆናቸው ልጃገረዶች በመንግስትና በግል ትምህርት ቤቶች በቀንም ሆነ በማታ ለሚማሩ ተማሪዎች እና ከትምህርት ገበታ ውጭ ለሆኑ ሴት ልጃገረዶች የሚሰጥ ሲሆን በሁሉም የመንግስት ጤና ተቋማት እና በሚዘጋጁ ጊዜያዊ ጣቢያዎች የሚሰጥ ይሆናል፡፡

አንዲት ዕድሜዋ 14 ዓመት የሆናት ሴት ልጅ የማህጸን በር ካንሰር መከላከያ ክትባትን 2 ጊዜ መውሰድ የሚገባት ሲሆን የመጀመሪያውን ክትባት በወሰደች ከ6 እስከ አንድ ዓመት ባለ ጊዜ ውስጥ ደግሞ ሁለተኛውን ክትባት መወሰድ ይጠበቅባታል፡፡

በጋምቤላና ቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልሎች ደግሞ ከጥር 24 እስከ 29 ቀን 2013 ዓ.ም የሚሰጥ መሆኑን ከተያዘው መርሃግብር ለማወቅ ተችሏል፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.