Fana: At a Speed of Life!

በሀገር ውስጥ አምራች የተመረተ 17 ሚሊየን ሊትር ዘይት ወደ ገበያ ገብቷል – የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር

አዲስ አበባ፣ የካቲት 22፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) 17 ሚሊየን ሊትር ዘይት በሀገር ውስጥ አምራች ኢንዱስሪትዎች ተመርቶ ወደ ገበያ መግባቱን የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስትር አቶ መላኩ አለበል የመሰረታዊ ሸቀጦች አቅርቦትና ፍላጎትን በማሟላት የህብረተሰቡን የኑሮ ሁኔታ ለማሻሻል በተሰራው ስራ የዘይት ፋብሪካዎች ተገንብተው በተያዘው የካቲት ወር ወደ ምርት በመግባት 17 ሚሊየን ሊትር ዘይት ወደ ገበያ ያስገቡ መሆኑን ነው የገለጹት፡፡

58 በመቶ ቀረጥና ተያያዥ ክፍያዎች ይጣልባቸው የነበሩ እንደ ዘይት፣ የህፃናት አልሚ ምግቦችና ሌሎች መሰረታዊ ምግብ ነክ ገቢ ምርቶች ወደ 5 በመቶ ዝቅ በማድረግ የገበያ የንግድ ስርዓቱን ለማሻሻል እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡

የኑሮ ውድነትን በቁጥጥር ክትትልና እርምጃ በመውሰድ ብቻ ማሻሻል አይቻልም ያሉት አቶ መላኩ ምርትና ምርታማነትን ከመቼውም ጊዜ በላይ በማሻሻል ፍላጎትና አቅርቦቱን ለማጣጣም መንግስት ለግብርናውና አምራች ኢንዱስትሪ ዘርፉ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ በመስራት ላይ መሆኑን ነው ያስረዱት፡፡

የኢትዮጵያ የሸቀጦች አማካኝ የዋጋ ንረት 19 ነጥብ 2 በመቶ መሆኑን የገለፁት  አቶ መላኩ መንግስት የንግድ ስርዓቱን በማዘመን፣ የአቅርቦትና ፍላጎት ልዩነቱን ለማጥበብና ምርትና ምርታማነት እንዲጨምር በማድረግ አማካኝ የዋጋ ንረቱን ወደ 13 በመቶ ዝቅ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.