Fana: At a Speed of Life!

በሁለተኛ ዙር የ40/60 ዕጣ የወጣላችሁ ባለዕድለኞች ከነገ ጀምሮ ቁልፍ ርክክብ ሊደረግ ነው

አዲስ አበባ፣ የካቲት 28፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በሁለተኛ ዙር 40/60 ዕጣ የወጣባቸውን ቤቶች ከፊታችን ሰኞ የካቲት 29/2013 ዓ.ም ጀምሮ በአፈፃፃማቸው የተሻሉ የግንባታ ሳይቶችን ለባለ ዕድለኞች ቁልፍ ርክክብ ለማድረግ የከተማ አስተዳደሩ ዝግጅት ዝግጅት ማጠናቀቁን አስታወቀ፡፡

ባለእድለኞችም ከፊታችን ሰኞ የካቲት 29/2013 ዓ.ም ጀምሮ በአፈፃፃማቸው የተሻሉ የግንባታ ሳይቶችን የአዲስ አበባ ከተማ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን በየቅርንጫፍ ጽቤቱ በሚያወጣው የጊዜ ሰሌዳ መሠረት የቤቶቹን ቁልፍ ለባለ ዕድለኞች ርክክብ የሚያደርግ ይሆናል።

በሚወጣው የጊዜ ሰሌዳ መሠረት ቁልፍ  የምትረከቡ  ባለ ዕድለኞች የቤቶቹን  ቀሪ የማጠናቀቂያ ሥራዎች ማሰራት የምትችሉ መሆኑን የከተማ አስተዳደሩ ከወዲሁ ይገልጻል።

በመጀመሪያ ዙር ላይ የተካተቱ 220 ህንፃዎች የሚገኙበት የግንባታ ሳይቶች ዝርዝር እንደሚከተለው ቀርቧል።

  1. መሪ ሎቄ (14 ህንፃዎች)
  2. እህል ንግድ (5 ህንፃዎች)
  3. ህንፃ አቅሪቢ (8 ህንፃዎች)
  4. አስኮ (13 ህንፃዎች)
  5. አያት 1 ሳይት 1 (14 ህንፃዎች)
  6. አያት 1 ሳይት 2 (38 ህንፃዎች)
  7. አያት 1 ሳይት 3 (41 ህንፃዎች)
  8. አያት 1 ሳይት 4 (39 ህንፃዎች)
  9. ሰሚት (8 ህንፃዎች)
  10. ቦሌ ቡልቡላ ሎት 1 (27 ህንፃዎች)
  11. ቦሌ ቡልቡላ ሎት 2 (13 ህንፃዎች)
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.