Fana: At a Speed of Life!

በሁመራ ከተማ በአንድ ሆቴል በተደረገ ፍተሻ ለሁለተኛ ጊዜ 37 ኩንታል አደንዛዥ እፅ ተገኘ

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 22 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በሁመራ ከተማ በአንድ ሆቴል በተደረገ ፍተሻ ለሁለተኛ ጊዜ 37 ኩንታል አደንዛዥ እፅ ተገኘ፡፡

በከተማዋ ህግን የማስከበር ግዳጅ እየተወጡ የሚገኙ የአማራ ክልል ፖሊስ አባላት ህገወጥ ድርጊቶችን ለማስወገድ እና የህዝብን ሠላም ለማስጠበቅ እየሠሩ መሆኑን የከተማዋ ፖሊስ መምሪያ ጊዜያዊ አስተባባሪ ኮማንደር ሙላት ማሞ ገልፀዋል።

ከአደንዛዥ እፁ በተጨማሪ በአንድ ሰው ስም የተመዘገቡ 11 የቤት ካርታዎች እና በዚሁ ግለሠብ ስም ከፍተኛ ገንዘብ የተዘዋወረበት ቼክ ተገኝቷል።

ከዚህ በተጨማሪም ገጀራዎች፣ መጥረቢያዎች እና ሌሎች መሳሪያዎች እንደተገኙ መናገራቸውን አብመድ ዘግቧል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል www.youtube.com/fanatelevision ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.