Fana: At a Speed of Life!

በህንድ በኮሮናቫይረስ ለህልፈት የተዳረጉ ሰዎች ቁጥር ከቻይና በለጠ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 21፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በህንድ በኮሮና ቫይረስ ለህልፈት የተዳረጉ ሰዎች ቁጥር ከቻይና በለጠ።

አሁን ላይ በህንድ የሟቾች ቁጥር 4 ሺህ 713  የደረሰ ሲሆን፥ በሃገሪቱ 165 ሺህ 829 ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል ነው የተባለው።

በህንድ በኮሮናቫይረስ ምክንያት የሚደርስ ሞት እና በቫይረሱ የሚያዙ አዲስ ሰዎች ቁጥር ከቻይና የበለጠ ሲሆን፥ በአገሪቱ በ24 ሰዓት ውስጥ ብቻ 175 አዲስ ሞት እና 7 ሺህ 466 አዲስ ሰዎች ቫይረሱ ተገኝቶባቸዋል።

በቻይና 165 ሺህ 799 ሰዎች በቫይረሱ ሲያዙ 4 ሺህ 711 ሰዎች ደግሞ ህይወታቸው አልፏል።

እንደ ጆን ሆፕኪንስ መረጃም በአለም 5 ሚሊየን 816 ሺህ 706 ሰዎች ቫይረሱ የተገኘባቸው ሲሆን፥ 362 ሺህ 102 የሚሆኑት ደግሞ ለህልፈት ተዳርገዋል።

2 ሚሊየን 583 ሺህ 4 ሰዎች ደግሞ ከቫይረሱ ማገገም ችለዋል።

እንዲሁም 53 ሺህ 971 ሰዎች በፅኑ ታመው የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸው ይገኛል።

ምንጭ፦ አልጀዚራ

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.