Fana: At a Speed of Life!

በህወሓት ጁንታ የተዘረፈው ንብረት መልሶ እንዲተካና ህዝቡ ተገቢ አገልግሎት እንዲያገኝ እንሰራለን- ዶ/ር ሙሉ ነጋ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 22፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በትግራይ ክልል በህወሃት ጁንታ የተዘረፈው ንብረት መልሶ እንዲተካና ህዝቡ ተገቢ አገልግሎት እንዲያገኝ የሚሰራ መሆኑን የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ዋና ሥራ አስፈጻሚ ዶክተር ሙሉ ነጋ ገለጹ።

የጊዜያዊ አስተዳደሩ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ዶክተር ሙሉ ነጋ፤ በሽሬ እንዳሥላሴ ከተማ ከነዋሪዎች ጋር በተደረገ ውይይይ ሕዝቡ ያመነበት አስተዳደር መቋቋሙን ገልጸዋል።

በዚህም ጊዜያዊ ከንቲባውን ጨምሮ የምክር ቤት አባላት እንዲሁም በከተማው አምስቱም ቀበሌዎች የሕዝብ መማክርት ጉባዔ አባላት መመረጣቸውን ገልጸዋል።

የወረዳና የቀበሌ ምክር ቤቶች ግን ወደ ቀደመው ሥራቸው እንዲመለሱ ዶክተር ሙሉ ጥሪ አቅርበዋል።

ምክር ቤቶቹ ደግሞ በቀበሌና በወረዳ ደረጃ ሕዝቡን የሚያስተዳድሩ አመራሮችን እንደሚመርጡ አብራርተዋል።

“በሕዝብ የተመረጠው ጊዜያዊ አስተዳደር የህወሃት ጁንታ ያጠፋቸው የመንግሥት መዋቅሮች ይዘረጋሉ” ብለዋል።

የወረዳውን በጀት በመጠቀምም የተዘረፈው የመንግሥትና የሕዝብ ንብረት እንደሚሟላ ጊዜያዊ ዋና ሥራ አስፈጻሚው ተናግረዋል።

ነዋሪዎች ከጊዜያዊ አስተዳደሩ ጎን በመሆን ለከተማና አካባቢው ሰላምና መረጋጋት እንዲሰሩም ዶክተር ሙሉ ጥሪ አቅርበዋል።

ከጊዜያዊ አስተዳደሩ ጋር በመተባበር ሰላምን ለማስጠበቅና የመንግሥት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ሥራ እንደሚጀምሩ በሚደረገው ጥረት ድርሻቸውን ለመወጣት ዝግጁ መሆናቸውን ነዋሪዎች ተናግረዋል።

የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደሩ ሌሎች አካባቢዎችም በሕዝብ የሚመረጥ ጊዜያዊ አስተዳደር እንደሚያደራጅ ዋና ሥራ አስፈጻሚው ማረጋገጣቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል www.youtube.com/fanatelevision ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.