Fana: At a Speed of Life!

በህገ ወጥ መንገድ ሲጓጓዝ የተገኘ 96 ኩንታል ቡና ተያዘ

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 26 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በምዕራብ ሸዋ ዞን ቶኬ ኩታዬ ወረዳ 96 ኩንታል ቡና ጭኖ በህገ ወጥ መንገድ ሲያጓጉዝ የተገኘ አሽከርካሪ መያዙን ፖሊስ አስታወቀ።
የወረዳው ፖሊስ አዛዥ ረዳት ኮማንደር ይገዙ ገብረሚካኤል ÷ አሽከርካሪው የተያዘው ንግድ ፈቃድም ሆነ ሌላ መስረጃ ሳይኖረው ቡናውን ከጅማ ጭኖ ወደ አዲስ አበባ ለማሳለፍ ሲሞከር መሆኑን ገልጸዋል።
ቡናው በወረዳው ጉደር ከተማ ንግድ ባንክ አካባቢ ትናንት ከሌሊቱ ስምንት ሰዓት ተኩል አካባቢ በኤፍ ኤስ አር ተሽከርካሪ እንደተጫነ በህብረተሰብ ጥቆማ መያዙን ገልጸዋል።
አሽከርካሪው የፖሊሶቹን እንቅሰቃሴ እንዳየ ለማምለጥ ቢሞክርም በቁጥጥር ስር ውሎ ጉዳዩ እየተጣራ መሆኑን ረዳት ኮማንደሩ አስረድተዋል።
ፖሊስ ሕገ ወጥ እንቅስቃሴን ለመከላከል በሚያደርገው ጥረት ኅብረተሰቡ አጥፊዎችን በመጠቆም የተለመደ ትብብሩን እንዲያሳይ አዛዡ ጠይቀዋል።
ወንጀልን በጋራ ለመከላከል ህብረተሰቡ ላደረገው ትብብርም ምስጋናማቅረባቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.