Fana: At a Speed of Life!

በህገ ወጥ መንገድ ድንበር የማሻገር ወንጀሎችን ለመመርመርና ለማስቀጣት የሚያስችል የአሰራር ስርዓት ሰነድ ተዘጋጀ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 14 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በህገ ወጥ መንገድ ድንበር የማሻገር ወንጀሎችን ለመመርመርና ለማስቀጣት የሚያስችል የአሰራር ስርዓት ሰነድ ተዘጋጅቶ በሲቪ ፖል የምስራቅ አፍሪካ፣ ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ እንዲሁም በፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን መካከል ርክክብ መደረጉን ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ አስታወቀ፡፡

ምክትል ጠቅላይ አቃቤ ህግ አቶ ፍቃዱ ፀጋ በሰዎች መነገድና ሰዎችን በህገ ወጥ መንገድ ድንበር ማሻገር ወንጀል የዓለም ሃገራትን እየተፈታተነ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ይህን ወንጀል ለመመርመርና ለማስቀጣት የሚያስችል ወጥ አሰራር መዘርጋቱ በተለይም ለመርማሪ ፖሊሶችና ለዐቃቢያነ ህግ ወንጀሉን ለመመርመር ብሎም በክስ ሂደት ውስጥ ከፍተኛ ጥቅም እንዳለውም ነው የተናገሩት፡፡

ስራውን ወጥ እና የተቀላጠፈ ለማድረግም የአሰራር ስርአቱ መዘርጋቱ ፋይዳው የጎላ እንደሚሆን ገልፀዋል፡፡

በጠቅላይ ዐቃቤ ህግ የንቃተ ህግ ትምህርትና ስልጠና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ እንዳልካቸው ወርቁ በበኩላቸው በሰዎች መነገድ እና ሰዎችን በህገ ወጥ መንገድ ድንበር የማሻገር ወንጀሎች በዋናነት የአሰራር ስርአቱ ወጥ የሆነና ተመሳሳይ አሰራር ለመዘርጋት ታስቦ መዘጋጀቱን ጠቁመዋል፡፡

በመድረኩ ላይ የአሰራር ስርአቱን በተመለከተ ገለጻና ማብራሪያ መደረጉን ከጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.