Fana: At a Speed of Life!

በልብ እና ደም ቧንቧ በሽታዎች የተያዙ ሰዎች በከፋ የኮቪድ-19 ቫይረስ የመያዝ እድላቸው የሰፋ ነው

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 11 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የፌደራል ጤና ሚኒስቴር እና ፖፑሌሽን ሰርቪስስ ኢንተርናሽናል የአስትራዜኒካ አካል ከሆነው ሄልዚ ኸርት አፍሪካ ፕሮግራም ጋር በመሆን የዘንድሮውን የአለም የደም ግፊት ቀን ጋር በተያያዘ በጋራ እየሰሩ መሆናቸው ተገለፀ።

የዚህ አመት መሪ ቃል ‘የደም ግፊትዎን በትክክል ይለኩ፣ ይቆጣጠሩ፣ ረዥም አመት ይኑሩ’  ነው ተብሏል።

የአለም የጤና ድርጅት በእድሜ የገፉ እና የልብ እና የደም ቧንቧ ህመም የመሳሰሉ ስር የሰደዱ የህክምና ህመሞች ያለባቸው ሰዎች በከፋ የኮቪድ-19  የመያዝ እድል እንዳላቸው ይገልፃል።

የፈረንጆቹ 2016ቱ የአለም ጤና ድርጅት ሀገራዊ ሪፖርት እንደሚገልፀዉ ኢትዮጵያ ውስጥ ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች ሀገሪቱ ውስጥ ካሉ ሞቶች 39 በመቶ ይይዛሉ ተብሎ ይገመታል።

ከእነዚህም መካከል 16 በመቶ በልብ እና በደም ቧንቧ በሽታ የሚመጡ ናቸው።

በ2015 በተካሄደዉ ስቴፕዋይዝ የዳሰሳ ጥናት 95 በመቶ የጥናቱ ተሳታፊዎች አንድ ወይም ሁለት ለተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች አጋላጭ መንስኤዎች እንደነበሯቸው ያመላከተ ሲሆን በኢትዮጵያ የበሽታዉ ጫናን ያሳየ መሆኑ ተጠቁሟል።

ባህሪያዊ የተጋላጭነት ምክንያቶች የፍራፍሬዎች እና አትክልቶች ዝቅተኛ አወሳሰድን ጨምሮ ጤናማ ያልሆነ አመጋገብ ፣ እንደ ፍራፍሬ እና አትክልቶች ዝቅተኛ መመገብ ፣ አካላዊ እንቅስቃሴ አለማድረግ ፣ ከመጠን በላይ የአልኮል መጠቀም ፣ ትምባሆ መጠቀም እና ከመጠን ያለፈ ውፍረትን ያካትታሉ።

“ከፍ ያለ የደም ግፊት ቀደም ብሎ ባልተለየባቸዉ ሁኔታዎች እንዲሁም ተገቢየሆኑ የትምህርት ፣ የመከላከልና የህክምና እርምጃዎች ካልተወሰዱ ከፍ ካለ  የደም ግፊት ጋር የተያያዙ የልብና የደም ቧንቧ በሽታዎች ለማከም እንደሚከብድ ተነግሯል።

ይህ ማለት ለመንግስትም ሆነ ከራሳቸው ኪስ መክፈል ለሚገባቸው ግለሰቦች የወጪ ሸክም መሆኑን  የፌዴራል ጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ደረጀ ዱጉማ  ገልፀዋል።

በተጨማሪ ሚኒስቴር ዴኤታው  “የደም ግፊት ወይም ከፍ ያለ የደም ግፊት ምንም ዓይነት የሕመም ምልክት ስለማያሳይ ዝምተኛ ገዳይ በመባል ይታወቃል፤ ስለሆነም ከፍ ላለ የደም ግፊት ቀድሞ መመርመር እንዲሁም ባህሪያዊ የተጋላጭነት ሁኔታዎችን መቀነስ አስፈላጊ ነው፡፡‘’ ሲሉ ነው የገለፁት።

ይህን አስመልክቶም መንግስት የተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች  ጫና ለመቀነስ የተለያዩ ፖሊሲዎችን ከመተግበር በተጨማሪ ስለ ደም ግፊት እና መንስኤዎቹ እውቀት ለመፍጠር ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ<ሄልዚ ኸርት አፍሪካ > ከመሰሉ ፕሮግራሞች ጋር በመተባበር የሚሰራ ሲሆን በሀገሪቱ ውስጥ ያለው የደምግፊት ተፅዕኖን በመቀነስ ረገድ በፕሮግራሞቹ የተጨመሩትን እሴቶች ያደንቃል።’’ ማለታቸውን  ለፋና ብደሮድካስቲንግ ኮርፖሬት በላኩት መግለጫ ላይ ገልፀዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.