Fana: At a Speed of Life!

በልደታ ክፍለ ከተማ በመቻሬ ሜዳ የታቦት ማደሪያ የፅዳት ዘመቻ ተካሄደ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 8 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ልደታ ክፍለከተማ በታቦት ማደሪያ ስፍራ በዓሉ የደመቀና ፅዱ እንዲሆን የተለያዩ የሃይማኖት አባቶች እና የአካባቢው ማህበረሰብ በተገኘበት የፅዳት ዘመቻ ተካሄደ፡፡

በዛሬው እለት በልደታ ክፍለከተማ መጪውን የጥምቀት በዓል ምክንያት በማድረግ በመቻሬ ሜዳ የፅዳት ዘመቻ ተካሂዷል፡፡

በዚህ የፅዳት ዘመቻ ላይ ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የመንግስት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት አስተባባሪ አቶ ጃንጥራር አባይ ለሁሉም ሃይማኖታዊ በዓሎቻችን ስኬትና ድምቀት የጋራ ሃላፊነት አለብን ብለዋል፡፡

ጥምቀት ኢትዮጵያ ካሏት የአደባባይ በዓላት አንዱና ዋነኛው መሆኑንም ተናግረዋል፡፡

ይህ በዓል የሁሉም የጋራ በዓል ነው ያሉ ሲሆን ኢትዮጵያውያን አንዱ የአንዱን በዓል በድምቀት የማክበር እና የማድመቅ ልማድ ያላቸው ድንቅ ህዝቦች ናቸው ብለዋል፡፡

ከፀጥታ አንፃርም በዓሉ በሰላም ተጀምሮ በሰላም እንዲጠናቀቅ መላው የከተማው ነዋሪ በተለመደው ኢትዮጵያዊ ጨዋነት እንዲያሳልፍና ከፀጥታ አካላት ጋር በቅርበትና በትብብር ይሰራ ዘንድ አቶ ጃንጥራር አባይ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል፡፡

የተለያየ እምነት ያላቸው የህብረተሰብ ክፍሎች በተሳተፉበት በዚህ የፅዳት እንቅስቃሴ ላይ አርቲስቶች፣ የሃይማኖት አባቶች እና የእምነት አባቶች እንዲሁም የአዲስ አበባ ፖሊስ አባላት ተሳትፎ አድርገዋል፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.