Fana: At a Speed of Life!

በሎስ አንጀለስ ማራቶን አትሌት ባየልኝ አሸናፊ ሆነ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 30፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ትናንት በሎስ አንጀለስ በተደረገ የማራቶን ውድድር ኢትዮጵያዊው አትሌት ባየልኝ ተሻገር አሸናፊ ሆኗል።
አትሌት ባየልኝ ርቀቱን 2 ሰዓት ከ8 ደቂቃ ከ26 ሰከንድ በመግባት አሸናፊ ሆኗል።
ኬንያውያኑ ጆን ላጋት እና ዊልሰን ቼቤት ደግሞ ሁለተኛ እና ሶስተኛ በመሆን ውድድራቸውን አጠናቀዋል።
የርቀቱ አሸናፊ አትሌት ባየልኝ 53 ሺህ ዶላር ሽልማት ተበርክቶለታል።
በሴቶች በተደረገ ውድድር ደግሞ አትሌት አልማዝ ነገደ 2 ሰዓት ከ32 ደቂቃ ከ28 ሰከንድ በመግባት ውድድሩን ሁለተኛ በመሆን አጠናቃለች።
በተያያዘ ዜና ትናንት በሆላንድ በተደረገ የግማሽ ማራቶን ውድድር ኢትዮጵያዊው አትሌት ዳዊት ወልዴ 1 ሰዓት ከ59 ደቂቃ ከ58 ሰከንድ በመግባት ርቀቱን በበላይነት አጠናቋል።

ምንጭ፦ bleacherreport.com/

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.