Fana: At a Speed of Life!

በሐረሪ ክልል ሦስተኛው ዙር የኮቪድ 19 መከላከያ ክትባት መሰጠት ጀመረ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 2 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በክልሉ እድሜያቸው ከ12 አመት በላይ የሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች በገጠር ቀበሌዎችና በከተማ ክትባት እየተሰጣቸው ነው።
እንደ ሐረሪ ክልል ባለፉት ሁለት ዙሮች እስካሁን ከ109 ሺህ በላይ ሰዎች ክትባቱን ወስደዋል።
በዚህ ዙርም ከ80 ሺህ ህዝብ በላይ ለመከተብ መታቀዱን የክልሉ ጤና ቢሮ ምክትል ሀላፊ አቶ ፈቲህ መሀዲ ተናግረዋል።
የኮቪድ 19 ወረርሽኝ በአሁኑ ወቅት ዳግም እየተስተዋለ ስለሚገኝ ህዝቡ ከክትባቱ ባሻገር ጥንቃቄ እንዲያደርግም ጥሪ አቅርበዋል።
ክትባትቱ ዛሬን ጨምሮ ለቀጣዮቹ 10 ቀናት በይፋ በመንግስት የጤና ተቋማት እንደሚሰጥ ተገልጿል።
በቲያ ኑሬ
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.