Fana: At a Speed of Life!

በሐረሪ ክልል በተደረገው ድንገተኛ ዘመቻ ለጥፋት ስራ ሊውሉ የነበሩ የጦር መሳሪያዎች ተያዙ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 16፣ 2013 (ኤፍቢሲ) በሐረሪ ክልል ባለፉት ሁለት ሳምንት በተደረገው  ድንገተኛ ፍተሻ ክላሽን ጨምሮ የጦር ሜዳ መነጽር፣ የተለያዩ ሀገራት ገንዘቦች፣ ወታደራዊ አልባሳት፣ ገጀራ፣ የእጅ ሽጉጦችና ብዛት ያላቸው ጥይቶች መያዛቸውን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡

የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር አቶ ጃብር አሊዪ በሰጡት መግለጫ 453 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ማዋሉንም ነው የገለጸው፡፡

ከተጠርጣሪዎቹ መካከል 212ቱ በምርመራ ላይ የሚገኙ ሲሆን ቀሪዎቹ ጉዳያችው ተጣርቶ መለቀቃቸውን ገልጸዋል፡፡

ግለሸቦቹ ከጁንታው ቡድን ጋር በቀጥታ ግንኙንት አላቸው ያሉት ምክትል ኮሚሽነሩ  የተገኘባችው ከአስር በላይ ላፕቶፖች ላይ ምርምራ ለመጀመር  በዝግጅት ላይ መሆናቸውንም ነው የጠቀሱት፡፡

በአንድ ግለስብ ስም ብቻ ከአንድ እስከ  አራት ሚሊየን ብር ገቢ ሲደርግለት መቆየቱን የያስረዱት ምክትል ኮሚሽነሩ ከ20 በላይ የባንክ ደብተሮችና ቼኮች መያዛቸውንም አስታውቀዋል፡፡

በተደረገው ድንገተኛ ዘመቻ ከሰራዊቱ የተሰናበቱ 22 አካላት ስም፣ ስልክ ቁጥራቸው እና ፊርማቸው ያረፈበት ሰነድ መገኘቱን የጠቆሙት ደግሞ በክልሉ ፖሊስ ኮሚሺን  ወንጀል መከላከል እና ትራፊክ ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት ኢንስፔክተር ወንደሰን ካሳሁን ናቸው፡፡

አክለውም ተወላጅነቱ በክልሉ ባልሆነ ግለሰብ ስም ሰባት መታወቂያ ወጥቶ መገኘቱን ነው ያነሱት፡፡

ሐረማያ ፋና ኤፍ ኤም በስፍራው ተገኝቶ ለማየት እንደሞከረው የተለያዩ ወታደራዊ የውጊያ መጽሃፍጽን ጨምሮ ላፕቶፖች፣ የተለያዩ ሰነዶች፣ የውጪ ሀገራት  ገንዘቦች፣ ሞባይሎች፣ ደብዳቤዎችና በመከላከያ የኦሮሚያ ልዩ ሃይል ወታደራዊ አልባሳት መያዛቸውን ተገንዝቧል፡፡

የሐረማያ ፋና ኤፍ ኤም በስፍራው ተገኝቶ ለማየት እንደሞከረው የተለያዩ ወታደራዊ የውጊያ መጸሃፎችን ጨምሮ ላፕቶፖች፣ የተለያዩ ሰነዶች ፣ የውጪ ሀገራት  ገንዘቦች፣ ሞባይሎች፣ ደብዳቤዎችና በመከላከያ የኦሮሚያ ልዩ ሃይል ወታደራዊ አልባሳት መያዛቸውን ተገንዝቧል፡፡

በእዮናዳብ አንዱዓለም

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.