Fana: At a Speed of Life!

በሐዋሳ ከተማ የድንጋይ ማውጫ ካባ ተደርምሶ የሁለት ሰዎች ህይወት አለፈ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 18፣ 2012(ኤፍ.ቢ.ሲ) በሐዋሳ ከተማ የድንጋይ ማውጫ ካባ ተደርምሶ የሁለት ሰዎች ህይወት አለፈ።

በከተማው ሐዌላ ቱላ ክፍለ ከተማ ሐዌላ ወንዶ ቀበሌ በደረሰው ናዳ ሁለት ሰዎች ሲሞቱ፥ ሶስት ሰዎች ደግሞ የአካል ጉዳት እንደደረሰባቸው የሀዋሳ ከተማ ፖሊስ መምሪያ አዛዥ ኮማንደር ኢዮብ አቤቶ ተናግረዋል።

ተጎጂዎች ወደ ሆስፒታል ተወስደው የሕክምና ክትትል እየተደረገላቸው መሆኑም ተጠቁሟል።

በሰው ላይ ከደረሰው ጉዳት ባሻገርም በንብረት ላይ ጉዳት መድረሱን ኮማንደር ኢዮብ ገልፀዋል።

በታደሰ ሽፈራው

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.