Fana: At a Speed of Life!

በመተከል ዞን ለተፈናቀሉ ዜጎች የተጀመረውን ድጋፍ ለማጠናከር ከከተማ አስተዳደሩ አመራሮች ጋር ውይይት ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 25፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልሉ ከፍተኛ አመራሮች በመተከል ዞን ለተፈናቀሉ ዜጎች የተጀመረውን ድጋፍ ለማጠናከር ከከተማ አስተዳደሩ አመራሮች ጋር ውይይት አካሂደዋል።

የአሶሳ ከተማ አስተዳደር አመራሮች፣ ባለሃብቶችና የተለያዩ የህብረተሠብ ክፍሎች በመተከል ዞን ለተፈናቀሉ ዜጎች ለሚደረገው የድጋፍ ማሠባሰቢያ መርሃ-ግብር ተሳትፎ እንዲያደርጉ ጥሪ ቀርቧል።

በመድረኩ የክልሉ ግብርናና የተፈጥሮ ሃብት ልማት ቢሮ ኃላፊና የክልሉ ርዕሰ- መስተደድር ተወካይ አቶ ባበክር ኸሊፋ በገቢ አሰባሰብን ዙሪያ ለከተማ አስተዳደሩ አመራሮች ኦሬቴሽን ሰጥተዋል።

አቶ ባበክር፣ በመተከል ዞን በተከሰተው የፀጥታ ችግር በርካታ ዜጎች ከቀያቸው መፈናቀላቸውን፣ የሰው ህይወት መጥፋቱንና ንብረት መውደሙን ጠቁመው ለወገን ደራሽ ወገን እንደመሆኑ መጠን ሁሉም ዜጋ የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ ጥሪ አቅርበዋል።

በዞኑ የተፈናቀሉ ዜጎችን በዘላቂነት ለማቋቋም በክልሉ ከተለያዩ የህበረተሰብ ክፍሎች 50 ሚሊዮን ብር ለመሰብሰብ ታቅዶ የተለያዩ አደረጃጀቶችን በመፋጠር እንቅስቃሴ ተጀምሯል ብለዋል።

እንደ አቶ ባበክር ገለጻ፣ በድጋፍ ማሰባሰቢው በከተማ አስተዳደሩ የሚገኙ መንግሥታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ እና በተለያዩ የሥራ ዘርፎች ላይ የተሰማሩ አካላት የነቃ ተሳትፎ እንዲያደርጉ ይጠበቃል።
የሚሰበሰበው ድጋፍ በካሽ እና በአይነት ለመሰብሰብ ዕቅድ መያዙንም አንስተዋል።

የአሶሳ ከተማ አስተዳደር አቶ ዑመር አህመድ፣ በመተከል ዞን በተከሰተው የፀጥታ ችግር የተጎዱ ዜጎችን መልሶ ለማቋቋም በሚደረገው ጥረት የከተማ አስተዳደሩ አመራሮና ሠራተኛ የበኩላቸውን ድርሻ እንዲወጡ ጠይቀዋል።

ሌሎች የከተማ አስተዳደሩ አመራሮሽ በበኩላቸው፣ በመተከል ዞን በተከሰተው የፀጥታ ችግር በዜጎች ላይ የደረሰውን የኢኮኖሚና የስነ-ልቦና ጫና በመቅርፍ በዘላቂነት ለማቋቋም የቀረበው የድጋፍ ማስባሰብ ኘሮግራም አስፈላጊና ወቅታዊ መሆኑን አንስተዋል።

የከተማ አስተዳደሩ አመራሮች ውይይት በማደረግ ከወር ደሞዛቸው የተፈናቀሉ ዜጎችን መልሶ ለማቋቋም የሚደረገውን ጥረት ለማገዝም ቃል ገብቷል።

የዜጎችን ህይወት ለመታደግ በሚደረገው የድጋፍ ማሰባሰብ ሁሉም ዜጋ የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ ጥሪ መቅረቡን ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.