Fana: At a Speed of Life!

በመተከል ዞን ማረሚያ ቤት ከሁለት ዓመታት በላይ ፍርድ ቤት ያልቀረቡ ተጠርጣሪዎች ተገኙ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 23፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የተቋቋመው የተቀናጀ ግብረ ኃይል በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን ማረሚያ ቤት ባደረገው ጉብኝት ከሁለት ዓመታት በላይ ፍርድ ቤት ያልቀረቡ ተጠርጣሪዎችን አገኘ።
ተጠርጣሪዎቹ ጉዳያቸው ታይቶ በሶስት ቀናት ውስጥ እልባት እንዲሰጣቸውም ግብረ ሃይሉ አሳስቧል።
ግብረ ሃይሉ በማረሚያ ቤት ባደረገው ጉብኝት ከ2011 ዓ.ም ጀምሮ በነበረ የፀጥታ ችግር በወንጀል ተጠርጥረው እስካሁን ፍርድ ቤት ያልቀረቡ ተጠርጣሪዎችን አግኝቷል።
ከፀጥታ ችግር ጋር ተያይዞ በወንጀል ተጠርጥረው ፍርድ ቤት ሳይቀርቡ ከሁለት ዓመት በላይ በማረሚያ ቤት መቆየታቸውንም አረጋግጧል።
በግብረ ኃይሉ የህግ ማስከበርና የፀጥታውን ዘርፍ በበላይነት የሚመሩት ሌተናል ጀኔራል አስራት ዴኔሮ ተጠርጣሪዎቹ ፍርድ ቤት ሳይቀርቡ ከሁለት ዓመታት በላይ መታሰራቸው ከህግ አግባብ ውጪ መሆኑን ገልጸዋል።
በዚህም ከፌደራል ዐቃቤ ህግ መርማሪ ቡድን ጋር ስራውን የሚመራ ኮሚቴ ተቋቁሞ በሚቀጥሉት ሶስት ቀናት ውስጥ ለማጠናቀቅ እያጣራ እንደሆነ መግለጻቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
ግብረ ኃይሉ በዞኑ ህግ የማስከበርና በወንጀል የተጠረጠሩ አካላት በህግ ተጠያቂ እንዲሆኑና የሰብዓዊ ድጋፍ የሚያስፈልጋቸው እርዳታ እንዲያገኙ እየሰራ መሆኑ ይታወቃል።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.