Fana: At a Speed of Life!

በመተከል ዞን በፀጥታ ችግር ተቋርጠው የነበሩ የልማት ፕሮጀክቶች ስራቸውን እንዲቀጥሉ ጥሪ ቀረበ

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 5፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በመተከል ዞን በፀጥታ ችግር ምክንያት ተቋርጠው የነበሩ የተለያዩ የልማት ፕሮጀክቶች ስራቸውን እንዲቀጥሉ የዞኑ የተቀናጀ ግብረ ሃይል ጥሪ አቅርቧል።

የመተከል ዞን የተቀናጀ ግብረሃይል አስተባባሪ ሌተናል ጄኔራል አስራት ዴኔሮ፣ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳደር ጌታሁን አብዲሳ እንዲሁም ሌሎች የግብረሃይሉ አመራሮች በግልገል በለስ ከተማ የንፁህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክትን ጎብኝተዋል።

ፕሮጀክቱ በመተከል ዞን ግልገል በለስ እና በማንዱራ ወረዳ ገነተ ማርያም ከተሞችን ተጠቃሚ የሚያደርግ የከርሰ ምድር ውሃ ፕሮጀክት ነው።

በሰላም ሚኒስቴር ድጋፍ በ85 ሚሊየን ብር ወጪ እየተገነባ የሚገኘው ፕሮጀክቱ የግንባታ አፈፃፀም 90 በመቶ ደርሷል።

በዞኑ በነበረው የፀጥታ ችግር ግንባታቸው ተጀምረው የተቋረጡ የውሃ፣ የትምህርትና ሌሎች 43 ፕሮጀክቶች መኖራቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.