Fana: At a Speed of Life!

በመተከል ዞን ችግር የተፈጠረው ጁንታው የህዳሴ ግድብ ግንባታን ለማስተጓጎል ከጥፋት ኃይሎች ጋር  ተቀናጅቶ በመንቀሳቀሱ ነው – ሌተናል ጄኔራል አስራት ዴኔሮ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 30፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በመተከል ዞን ችግር የተፈጠረው ጁንታው ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታን ለማስተጓጎል ከጥፋት ኃይሎች ጋር ተቀናጅቶ በመንቀሳቀሱ እንደነበር የመተከል ዞን የተቀናጀ ግብረ ኃይል ዋና አስተባባሪ ሌተናል ጄኔራል አስራት ዴኔሮ ተናገሩ።

በዞኑ የጉባ ወረዳ ነዋሪዎች በአካባቢው ዘላቂ ሰላም እንዲሰፍን የበኩላቸውን ጥረት እንደሚያደርጉ አረጋግጠዋል።

በዞኑ የተቋቋመው የተቀናጀ ግብረ ኃይል ከነዋሪዎቹ ጋር  ተወያይቷል።

ነዋሪዎቹ ከግብረ ኃይሉ አመራር ጋር በተካሄደው ውይይት ላይ እንዳረጋገጡት፤ በአካባቢያቸው ዘላቂ ሰላም ለማስፈን ሚናቸውን ይወጣሉ።

ግብረ ኃይሉ በዞኑ ከተቋቋመ ወዲህ የወረዳው ሰላምና ፀጥታ መሻሻል እንደታየበት መስክረዋል።

ከግብረ ኃይሉ ጋር በመቀናጀትም ዘላቂ ሰላም ለማስፈን እንደሚተጉ ተናግረዋል።

የመተከል ዞን የተቀናጀ ግብረ ኃይል ዋና አስተባባሪ ሌተናል ጄኔራል አስራት ዴኔሮ መንግሥት የአካባቢውን የፀጥታ ችግር ለመፍታት እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል።

ወደ ልማት ለመግባትም ጥረት እየተደረገ እንደሆነ አመልክተዋል።

በአካባቢው ችግር የተፈጠረው ጁንታው ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታን ለማስተጓጎል ከጥፋት ኃይሎች ጋር  ተቀናጅቶ በመንቀሳቀሱ እንደነበር አስረድተዋል።

ህብረተሰቡም አንድነቱን በማጠናከር ሰላምን ማረጋገጥና ለልማት መትጋት እንዳለበት አስገንዝበዋል።

ግብረ ኃይሉ በአካባቢው ዘላቂ ሰላም እስኪረጋገጥ ጥረቱን እንደማያቋርጥ ሌተናል ጄኔራል አስራት አረጋግጠዋል።

በሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማዕከል አስተባበሪ አቶ ተስፋዬ ቤልጂጌ በበኩላቸው ህብረተሰቡ በአካባቢው ዘላቂ ሰላም እንዲሰፍን አንድነቱን እንዲያጠናከር አሳስበዋል።

አንድነታችንን የምናረጋግጥ ከሆነ ሰላማችንን የሚያደፈርስ አካል አይኖርም ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.