Fana: At a Speed of Life!

በመተከል ዞን የሚስተዋሉ የጸጥታ ችግሮችን በዘላቂነት ለመፍታት በሁሉም ወረዳዎች የአመራር ግምገማ ከነገ ጀምሮ ይካሄዳል

አዲስ አበባ ፣ መስከረም 12 ፣2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በመተከል ዞን የሚስተዋሉ የጸጥታ ችግሮችን በዘላቂነት ለመፍታት ከነገ ጀምሮ በሁሉም ወረዳዎች የአመራር ግምገማ እንደሚካሄድ ተገልጿል።

በቅርቡ የጸጥታ ችግር የተፈጠረባቸውን ወምበራና ቡለን ወረዳዎች ጨምሮ በመተከል ዞን ሁሉም ወረዳዎች ዘላቂ ሠላምን ለመገንባትና የልማት ሥራዎችን አጠናክሮ ለማስቀጠል ያለመ የአመራር ግምገማ እንደሚካሄድ ነው የክልሉ መንግስት ያስታወቀው።

በዚህም በዞኑ ሁሉም ወረዳዎች የሚገኙ የመንግስትና የፓርቲ መዋቅሮችን በአግባቡ በመገምገም፣ የመዋቅር ማስተካከያ እና መልሶ የማደራጀት እርምጃዎች ይወሰዳሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ከክልሉ ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

#FBC
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.