Fana: At a Speed of Life!

በመተከል ዞን የተፈናቀሉ ዜጎችን ለማቋቋም የሚሠራ ክልል አቀፍ የገቢ አሰባሳቢ ኮሚቴ ተቋቋመ

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 22 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን በተፈጠረው የጸጥታ ችግር ከቀያቸው የተፈናቀሉ ዜጎችን በዘላቂነት ለማቋቋም የሚሠራ ክልል አቀፍ የገቢ አሰባሳቢ ኮሚቴ ተቋቁሟል፡፡
የክልሉ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ መለሰ በየነ÷ የክልሉ መንግሥት ከፌደራል መንግስትና ሌሎች ተባባሪ አካላት ጋር በመሆን በመተከል ዞን በተከሰተው የጸጥታ ችግር ምክንያት ለተፈናቀሉ ዜጎች ሰብዓዊ ድጋፍ በማድረግ ላይ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ለተፈናቀሉ ዜጎች አሁን እየተደረገ ካለው ሠብዓዊ ድጋፍ ባሻገር በዘላቂነት ለማቋቋም ክልል አቀፍ የገቢ አሰባሳቢ ኮሚቴ መዋቀሩን አቶ መለሰ ተናግረዋል።
ኮሚቴው በክልሉ በተለያዩ የኢንቨስትመንት ዘርፎች የተሰማሩ ባለሃብቶችን፣ መንግስታዊ የሆኑና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶትን እና የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎችን በማሳተፍ ለተፈናቀሉ ዜጎች የሚውል ድጋፍ እንደሚያሰባስብም ነው ኃላፊው ያስታወቁት።
ሀላፊው አያይዘውም የተቋቋመው ክልል አቀፍ የተፈናቃዮች ገቢ አሰባሳቢ ኮሚቴ ዝርዝር ዕቅድ በማውጣት በአጭር ጊዜ ወደ ስራ የሚገባ ሲሆን÷ የተፈናቀሉ ዜጎችን ካሉበት ችግር ለመታደግ እና በዘላቂነት ለማቋቋም በትኩረት ይሰራልም ብለዋል።
የድጋፍ አሰባሳቢ ኮሚቴው በክልሉ ሁሉም አካባቢዎች የገቢ ማሰባሰብ ሥራውን እንደሚሠራም አስታውቀዋል።
ኮሚቴው በቀጣይ የሚያሳውቃቸውን የገቢ ማሰባሰቢያ መንገዶችን በመጠቀም ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል ለተፈናቀሉ ዜጎች የበኩሉን ድርሻ እንዲያበረክትም ጥሪ ማቅረቡን ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.