Fana: At a Speed of Life!

በመተከል የሚንቀሳቀሱ የጁንታው ርዝራዦች እጅ እንዲሰጡ ማሳሰቢያ ተሰጠ

አዲስ አበባ ፣ህዳር 22 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን የጁንታው ህወሓት ጥፋት አስፈጻሚ ርዝራዦች ከጥፋታቻው በመታቀብ በአጭር ቀናት ውስጥ እጃቸውን ለዞኑ ኮማንድ ፖስት እንዲሰጡ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አሳሰቡ።
ርዕሰ መስተዳድሩ አቶ አሻድሊ ሃሰን ህዝብን ከህዝብ ሲያጋጭ የኖረው ጁንታው የህወሓት ቡድን መከላከያ ሠራዊት በከፈለው መስዋዕትነት ህልውናው አክትሟል ብለዋል፡፡
የጁንታውን የጥፋት ተልዕኮ አስፈጻሚዎች ለዓመታት በመተከል ባደረሱት ጥፋት ንጹሃን ሰዎች እንዲሞቱ፣ እንዲሰደዱና ንብረት እንዲወድም ምክንያት ሆኗልም ነው ያሉት፡፡
በዞኑ የህግ የበላይነትን ለማረጋጥ የጸጥታ ሃይሎች፣ ከአጎራባች አማራና ከፌደራል መንግስት ጋር በቅንጅት እየሰሩ መሆኑን በመግለጽ÷ በርካታ የጥፋት ቡድኑ ተላላኪዎች መደምሰሳቸውን አስታውቀዋል፡፡
እርምጃው እየተወሰደ ቢሆንም ጥፋቱ እስከ ቅርብ ጊዜ መቀጠሉን አቶ አሻድሊ ጠቁመዋል፡፡
“ህወሓት ስልጣንን በሃይል መልሶ ለመያዝ ያሰበው አልተሳካም” ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ÷ ለጁንታው ያልጠቀመው አካሄድ ለተላላኪዎችም እንደማይጠቅም ሊረዱ እንደሚገባም ነው የገለጹት።
በዞኑ የሚገኙ ቀሪ የጁንታው ርዝራዦች በቀጣይ ጥቂት ቀናት ለአካባቢው ኮማንድ ፖስት፣ በየደረጃው ለሚገኙ የጸጥታ አስከባሪዎችና ለሀገር ሽማግሌዎች በሠላም እጃቸውን እንዲሰጡም አሳስበዋል፡፡
ለጥፋት ቡድኑ የቀረበው ጥሪ የህዝብና የሀገር ደህንነትን በማስቀደም እንደሆነ ጠቁመው÷ የጥፋት ቡድኑ ተላላኪዎችም ጥሪውን ቢተገብሩ ተጠቃሚ እንደሚሆኑ አስታውቀዋል፡፡
“ይህ ካልሆነ ግን እንደ ጁንታው ለአንድ ጊዜና ለመጨረሻ ጊዜ የመደምሰስ እጣ ፈንታ ይገጥማቸዋል” ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል www.youtube.com/fanatelevision ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.