Fana: At a Speed of Life!

በመንግስት የተላለፉ ውሳኔዎችን በማያከብሩ ነጋዴዎች ላይ እርምጃ ይወሰዳል- ኢ/ር ታከለ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 28፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አትክልት ተራ ወደ ጃንሜዳ እንዲዛወር በወሰነው መሰረት ጃንሜዳን የማዘጋጀት ስራው መጠናቀቁን ኢንጅነር ታከለ ኡማ ገለፁ።

ምክትል ከንቲባ ኢንጅነር ታከለ ነጋዴዎችና በችርቻሮ ንግድ ላይ የተሰማሩ ዜጎችም መንግስት የህብረተሰቡን ጤና ለመጠበቅ የወሰነውን ውሳኔ ማክበር ይኖርባቸዋል ብለዋል።

የተወሰኑ ውሳኔዎችን በጥብቅ ዲሲፕሊን ይመራሉ፤ እርምጃዎችንም መወሰድ ጀምረናል ብለዋል ኢንጅነር ታከለ ኡማ።

አትክልት ተራ ከነገ ጀምሮ እንደሚዘጋ የገለፁት ምክትል ከንቲባው በጃንሜዳ የተዘጋጀው የአትክልት ግብይት ቦታ ሥራ ይጀመራልም ነው ያሉት።

በመሆኑም ነጋዴዎች በህግና መመሪያ እንዲመሩ ያሳሰቡ ሲሆን ነዋሪዎችም ህግን የማስከበር ስራው ተባባሪ ሆነው ጃንሜዳ በመሄድ እንዲገበያዩ አሳስበዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.