Fana: At a Speed of Life!

በመዲናዋ ሀገር አቀፍ የኅብረት ስራ ዐውደ ርዕይ እና ባዛርና ሊካሄድ ነው

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 2 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ)  በአዲስ አበባ ሀገር አቀፍ የኅብረት ስራ ዐውደ ርዕይ ፣ ባዛርና ሲምፖዚየም ሊካሄድ ነው።

የፌደራል ኅብረት ሥራ ኤጀንሲ በላከልን መግለጫ ÷ ዝግጅቱ “የኅብረት ሥራ ግብይት ለዘላቂ ሠላም” በሚል መሪ ቃል ከመጋቢት 9 እስከ 13 ቀን 2013 ዓ.ም  እንደሚካሄድ  አስታውቋል፡፡

የኅብረት ሥራ ማኅበራት  ለማህበራዊ፣ ለምጣኔ ኃብታዊ እና ለዘላቂ ሠላም ዕድገት የሚያበረክቱትን እና እያበረከቱ  ያሉትን አዎንታዊ አስተዋጽኦ የሚወሳበት እና የሚዘክርበት መልካም አጋጣሚ ነውም  ተብሏል፡፡

አቶ ኡስማን ሱሩር የፌደራል ኅብረት ሥራ ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር÷ለዘላቂ ሠላም መረጋገጥ ኅብረት ስራ ማኅበራት ምቹ መደላድሎች ናቸው  ብለዋል፡፡

ከመጋቢት 9 ቀን ጀምሮ ለ5 ተከታታይ ቀናት ቆይታ በሚኖረውና አምራች ህብረት ሥራ ማህበራትን ከሸማቾች በቀጥታ በማገናኘት ከ80 በላይ የሚሆኑ የኢትዮጵያ  ኅብረት ሥራ ማኅበራት ከ500 አይነት በላይ ምርታቸውን ይዘው ይቀርባሉ፡፡

በዐውደ ርዕዩና  ባዛሩ ዋዜማ መጋቢት 8 ቀን 2013 ሲምፖዚየም የዘርፉ ተሞክሮዎችን አዳዲስ አሰራሮች፣ ቴክኖሎጂዎች፣ ልምዶችና እውቀቶችን ለታዳሚው እንደሚቀርቡ የፌደራል ኅብረት ስራ ኤጀንሲ የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት መረጃ ያመልክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.