Fana: At a Speed of Life!

በመዲናዋ “ምክንያታዊ ወጣት ለሀገር ብልፅግና” በሚል መሪ ቃል በሺዎች የሚቆጠሩ ወጣቶች የሚሳተፉበት ስልጠና መሰጠት ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ ጥር 18፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ምክንያታዊና በሀሳብ ልዕልና ሞጋች ወጣቶችን በአስተሳሰብ ፣ በአመለካከት እና በተግባር በመፍጠር የተጀመረው አገራዊ ብልፅግና ለማረጋገጥና ተጠቃሚ ለማድረግ ያግዛል የተባለ የማይንድ ሴት ስልጠና ለወጣቶች መሰጠት ተጀመረ ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ‘‘ምክንያታዊ ወጣት ለሀገር ብልፅግና’’ በሚል መሪ ቃል በወጣቶች የስራ ዕድል ፈጠራ የአመለካከት ለውጥ የሚያመጣ የማይንድ ሴት ስልጠና በከተማዋ ለተውጣጡ 2 ሺህ ወጣቶች በቦሌ ክፍለ ከተማ ዛሬ በይፋ አስጀምሯል ።

በመክፈቻ መርሃ ግብሩ የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ፣ የስራ ኢንተርፕራይዝና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ሃላፊ አቶ ጃንጥራር አባይ ፥ ” ወጣቶች ያላቸውን እምቅ አቅምና የተሻገረ ህልም እውን በማድረግ በስራ ዕድል ፈጠራ ሚናቸውን እንዲወጡና ተጠቃሚ እንዲሆኑ መሠል የማይንድ ሴት የአመለካከትና የአስተሳሰብ ለውጥ ስልጠናዎች ተጠናክረው መቀጠል አለባቸው ብለዋል፡፡

ስልጠናው በቀጣይ በሁሉም ክፍለ ከተሞች እስከ ወረዳ 10 ሺህ ወጣቶች እንደሚሳተፉ ከከተማው ከንቲባ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.