Fana: At a Speed of Life!

በመዲናዋ በትራፊክ አደጋ ሳቢያ ይደርስ የነበረው ሞት 13 በመቶ ቀነሰ

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 16 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)በአዲስ አበባ ከተማ በትራፊክ አደጋ ሳቢያ ይደርስ የነበረውን ሞት 13 በመቶ መቀነስ መቻሉን የከተማዋ ትራፊክ ማኔጅመንት ኤጀንሲ ገለጸ።
ኤጀንሲው የትራፊክ አደጋን ለመቀነስ የሚያስችል የመንገድ ደህንነት ስትራቴጂን በመንደፍ ወደ ትግበራ መግባቱ ታውቋል ።
ስትራቴጂው ተግባራዊ በመደረጉና በየዓመቱ በትራፊክ ግጭት ሳቢያ የሚደርሰውን ሞት እና የአካል ጉዳት ለመቀነስ በተደረገ ጥረት በ2013ዓ.ም ከአምና ተመሳሳይ ወቅት ከነበረው በ13 በመቶ በመቀነስ የ59 ሰዎችን ህይወት ከሞት መታደግ መቻሉን ተገልጿል ።
በተመሳሳይ በትራፊክ ግጭት ከባድ የአካል ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች ቁጥር ዘንድሮ 1ሺህ 824 ሲሆን በ2012ዓ.ም 1 ሺህ 847 መሆኑን ከአዲስ አበባ ፕሬስ ሴክሬቴሪያት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
በዚህም 1 ነጥብ 25 በመቶ ወይም 23 ሰዎችን ከከባድ የአካል ጉዳት መታደግ ሲቻል÷ በአጠቃይ በበጀት ዓመቱ 1 ሺህ 824 ሰዎች ላይ ከባድ የአካል ጉዳት ደርሷል፡፡
በተጨማሪም 994 ሰዎች ላይ ቀላል የአካል ጉዳት የደረሰ ሲሆን ÷ 389 ሰዎች ደግሞ ለህልፈት ተዳርገዋል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.