Fana: At a Speed of Life!

በመዲናዋ በነገው እለት በፕሮጀክት ምረቃ ምክንያት የተወሰኑ መንገዶች ለተሽከርካሪ ዝግ ይሆናሉ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 5 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የመስቀል አደባባይ እና እስከ ማዘጋጃ ቤት የተከናወነው የመንገድ ግንባታ ምረቃ ምክንያት በማድረግ በነገው እለት የተወሰኑ መንገዶች ለተሽከርካሪ ዝግ እንደሚሆኑ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡

የመስቀል አደባባይ ግንባታ እና ከመስቀል አደባባይ እስከ ማዘጋጃ ቤት (የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሲከናወን የቆየው መንገዶችን የማስፋትና የማስዋብ ስራ ተጠናቆ ነገ ይመረቃል፡፡

የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽንም የምረቃ ስነ ስርዓቱ በሰላም እንዲጠናቀቅ ከሌሎች የፀጥታ እና ጉዳዩ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት እየሰራ መሆኑን ገልጿል፡፡

በከተማዋ በተለያዩ ጊዜያት የተካሄዱ ልዩ ልዩ ኩነቶች በሰላም የተጠናቀቁት ሰላም ወዳዱ ነዋሪ ለፀጥታ ስራ አስፈላጊውን ድጋፍ በማድረጉ መሆኑን የጠቀሰው ፖሊስ ለነዋሪዎች ምስጋናውን በማቅረብ ይህ የምረቃ ስነ ስርዓትም በሰላም እንዲጠናቀቅ ህብረተሰቡ የተለመደ ትብብሩን እንዲያደርግ ጠይቋል፡፡
በመሆኑም የምረቃ ስነ ስርዓቱ ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ ድረስ

ከጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን የላይኛው አደባባይ -ፒያሳ ጣሊያን ሰፈር መግቢያ – ሶማሌ ተራ አካባቢ የሚገኘው አደባባይ- አቡነ ጴጥሮስ አደባባይ -ጎላ ሚካኤል- ጥቁር አንበሳ ሼል – ሚቲዮሮሎጅ- ጎማ ቁጠባ -ሜክሲኮ ሰንጋ ተራ – ለገሃር ጉምሩክ መብራት – ቡናና ሻይ – ገነት መብራት – 4ኛ ክፍለ ጦር (ጥላሁን አደባባይ) – ቂርቆስ መታጠፊያ -አጎና ሲኒማ፤

ኦሎምፒያ – ኡራኤል አደባባይ – ባምቢስ መታጠፊያ- ካዛንቺስ ሼል -ፍልውሃ ሸራተን አካባቢ መስጊድ – ኦርማ ጋራዥ – ንግድ ማተሚ ቤት – ራስ መኮንን ድልድይ – አፍንጮ በር ፤

ከቀኑ 8 ሰአት ሰዓት ጀምሮ ለተሽከርካሪ ዝግ እንደሚሆን አሽከርካሪዎች ተገንዝበው አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀሙ እና የጋራ ለሆነው ሰላማችን አስፈላጊውን ትብብር እንዲደርጉ መልዕክቱን አስተላልፏል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.