Fana: At a Speed of Life!

በመዲናዋ በጥቃቅንና አነስተኛ ለተደራጁ አንቀሳቃሾች ከ2 ቢሊየን ብር በላይ የገበያ ትስስር ተፈጥሯል

አዲስ አበባ፣ የካቲት 5፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ የስራ እድል ፈጠራ እና ኢንተርፕራይዝ ልማት ቢሮ በጥቃቅንና አነስተኛ ለተደራጁ አንቀሳቃሾች የ2 ነጥብ 125 ቢሊየን ብር የሀገር ውስጥ የገበያ ትስስር መፍጠሩን ገለጸ።

ቢሮው ባለፉት ስድስት ወራት በ10 ሺህ 16 ኢንተርፕራይዞች ለታቀፉ 51 ሺህ 63 አንቀሳቃሾች 2 ነጥብ 125 ቢሊየን ብር የሀገር ውስጥ የገበያ ትስስር በመፍጠር ተጠቃሚ ማድረጉን አስታውቋል።

ከሀገር ውስጥ የገበያ ትስስር በተጨማሪም ኢንተርፕራይዞች በውጭ ገበያ ተሳታፊ እንዲሆኑ በማድረግ 11 ነጥብ 8 ሚሊየን ብር የውጭ ሀገር የገበያ ትስስር መፍጠሩንም ገልጿል።

ዚህ ባለፈም በበጀት ዓመቱ 6 ወራት ከ112 ሺህ በላይ ስራ ፈላጊ ወጣቶችን በመመዝገብ ለ104 ሺህ 587 ወጣቶች የስራ እድል በመፍጠር ተጠቃሚ ማድረጉን ከአዲስ አበባ ከተማ ፕሬስ ሴክሬታሪያት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.