Fana: At a Speed of Life!

በመዲናዋ አራት የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክቶች ተመረቁ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 23፣2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በአዲስ አበባ ሲገነቡ የነበሩ አራት የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክቶች ተመረቁ።

ከተመረቁት የመንገድ ፕሮጀክቶች ውስጥ 3ነጥብ3 ኪሎ ሜትር ርዝመትና 30 ሜትር ስፋት ያለው ከአራብሳ ኮንዶሚኒየም—አያት ኮንዶሚኒየም እንዲሁም 2ነጥብ1 ኪሎ ሜትር እና 20 ሜትር ስፋት ያለው ከሲ.ኤም.ሲ—አያት የተገነቡት መንገዶች ይገኙበታል።

እንዲሁም ከገርጂ— ኢትዮ ፓረንት ስኩል እና ከጅቡቲ ኤምባሲ— ሰሚት የተገነቡት መንገዶችም በዛሬው እለት ተመርቀዋል።

በዛሬው እለት ከተመረቁት መንገዶች ውስጥም ሁለቱ መጋቢ መንገዶች ናቸው ነው የተባለው።

በምርቃት መርሀግብሩ ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ኢ/ር ታከለ ኡማ የከተማ አስተዳደሩ ለትራንስፖርት ዘርፉ አማራጭ የሚፈጥሩና መኖሪያ አካባቢዎችን ከዋና መንገዶች ጋር የሚያገናኙ መጋቢ መንገዶች ላይ ትኩረት አድርጎ እየሰራ ነው ብለዋል።

በቅርብ ጊዜያትም በከተማዋ የክፍያ መንገዶች አገልግሎት እንደሚጀመርም ኢ/ር ታከለ የተናገሩ ሲሆን በመገናኛ አካባቢ የሚታየውን መጨናነቅ የሚቀንስ ግዙፍ ተርሚናል የሚገነባ መሆኑን መጠቆማቸውን ከአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.