Fana: At a Speed of Life!

በመዲናዋ በህገ ወጥ የመሬት ወረራና ግንባታ ላይ እርምጃ መውሰድ ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 6፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እየተስተዋለ ባለው ህገ ወጥ የመሬት ወረራና ግንባታ ላይ እርምጃ መወሰድ መጀመሩን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ኢንጅነር ታከለ ኡማ አስታወቁ።

በከተማዋ በተለይም በማስፋፊያ ክፍለ ከተምች ላይ እየተዛመተ የመጣውን የመሬት ወረራ ለማስቆም ከባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት የተወረሩ መሬቶችን የማስመለስ ስራ ተጀምሯል ብለዋል ምክትል ከንቲባው።

በዚህ መሰረት በዛሬው ዕለት በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ በህገወጥ መንገድ የተወረረና ግንባታ የተካሄደበትን 15 ሄክታር መሬት ወደ አካባቢ ጥበቃ ይዞታ መካተቱን ገልፀዋል።

ምክትል ከንቲባው በቀጣይም በህገ ወጥ መልኩ ግንባታ የተከናወነባቸው ቦታዎችን የማስመለስ ስራዎች ከህጋዊ ተጠያቂነት ጋር በተጠናከረ መልኩ እንደሚሰራ አስታውቀዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.