Fana: At a Speed of Life!

በመዲናዋ የሚስተዋለውን የትራንስፖርት እጥረት ለመፍታት በትራንስፖርት ዘርፍ ከተሰማሩ ማህበራት ጋር ምክክር ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ጥር 13፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)በአዲስ አበባ ከተማ የሚስተዋለውን የትራንስፖርት እጥረት ለመፍታት በትራንስፖርት ዘርፍ ከተሰማሩ ማህበራት ጋር ምክክር ተካሂዷል፡፡

በምክክር መድረኩ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የመንግሰት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት አስተባባሪ አቶ ጃንጥራር አባይ፣ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የማዘጋጃ ቤት አገልግሎት ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ጥራቱ በየነ፣ የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ ሃላፊ ኢንጂነር ስጦታው አከለ እና ሌሎች ከፍተኛ አመራሮች ተሳትፈዋል፡፡

በተጨማሪም በትራንስፖርት ዘርፍ ከተሰማሩ የታክሲ ተራ አስከባሪ ማህበራት ፣የላዳ፣መደበኛ ታክሲ እና የመካከለኛ አውቶቡሶች አሽከርካሪዎች ማህበራት ተወካዮች በተገኙበት የውይይት መድረክ መካሄዱ ነው የተነገረው፡፡

በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የመንግሰት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት አስተባባሪ አቶ ጃንጥራር አባይ እንደገለጹት ነዋሪዎቹ ምቹ፣ ዘመናዊና የተቀላጠፈ የትራንስፖርት አገልግሎት ይሻል ያሉ ሲሆን፤ ለዚህም ከብዙሃን ትራንስፖርት ጀምሮ የላዳ ታክሲ እና መደበኛ የታክሲ ማህበራትእንዲሁም በዘርፉ የተሰማሩ ባለሀብቶች የድርሻውን ሊወጣ እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡

አሁን ያለውን የትራንስፖርት እጥረት ለማቃለል ከተማ አስተዳደሩ ካሰማራቸው የብዙሃን ትራንስፖርት አውቶቡሶች በተጨማሪ ከፍተኛ በጀት በመመደብ ድጋፍ ሰጪ አውቶቡሶችን በመከራየት ወደ ስራ ተገብቶ አበረታች ለውጥ መታየቱን ሃላፊው መግለጹን ከከተማ አስተዳደሩ ፕረስ ሴክሬታሪ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.