Fana: At a Speed of Life!

በመዲናዋ የሚካሄደውን የኢፍጠር ስነ-ስርዓት አስመልክቶ ዝግ የሆኑ መንገዶች ይፋ ተደረገ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 3 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)በመዲናዋ ከባምቢስ እስከ ሜክሲኮ አደባባይ የሚካሄደውን የኢፍጠር ስነ-ስርዓት አስመልክቶ የትራፊክ መጨናነቅ እንዳይፈጠር ዝግ የሆኑ መንገዶችን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ይፋ አድርጓል።

ኮሚሽኑ 1442ኛ የረመዳን ጾምን አስመልክቶ በአዲስ አበባ ከተማ የኢፍጠር ስነ-ስርዓት ለማካሄድ ዝግጅቱ ተጠናቋል ብሏል፡፡

የኢፍጠር ፕሮግራሙ በሰላም እንዲከናወን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስፈላጊውን ዝግጅት አጠናቆ ወደ ስራ መግባቱንም አስታውቋል፡፡

ፕሮግራሙ ከባምቢስ እስከ ሜክሲኮ አደባባይ ባለው ጉዳና ላይ የሚካሄድ በመሆኑ በወቅቱ የትራፊክ መጨናነቅ እንዳይፈጠር ፡-

  • ከቅዱስ ኡራኤል ወደ መስቀል አደባባይ
  • ከኦሎምፒያ ወደ መስቀል አደባባይ
  • ከአራተኛ ክፍለ ጦር ወደ መስቀል አደባባይ
  • ከከፍተኛው ፍ/ቤት ፣ በለገሃር ወደ መስቀል አደባባይ
  • ከጎማ ቁጠባ ወደ መስቀል አደባባይ
  • ከአራት ኪሎ ወደ መስቀል አደባባይ
  • ከካዛንቺስ ወደ መስቀል አደባባይ
  • ከጥቁር አንበሳ ሼል ወደ መስቀል አደባባይ
  • ከቴዎድሮስ አደባባይ ወደ መስቀል አደባባይ
  • ከንግድ ማተሚያ ቤት ወደ መስቀል አደባባይ
  • ከሜትሮሎጂ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስዱ መንገዶች ፕሮግራሙ ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ ድርስ ዝግ መሆኑን ኮሚሽኑ ገልፆ አሽከርካሪዎች ሌሎች አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀሙ መልዕክት ማስተላለፉን ከአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.