Fana: At a Speed of Life!

በመዲናዋ የሚገኙ ባንኮች ወጣቶችን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ስራዎች ላይ ለመሳተፍ ዝግጅት እያደረጉ ነው

አዲስ አበባ፣ጥር 7፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ ባንኮች ወጣቶችን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ስራዎች ላይ ለመሳተፍ የያዙት እቅድን ለመጀመር ዝግጅት እያደረጉ መሆኑ ተገለጸ።

የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ኢንጅነር ታከለ ኡማ ከሁሉም ባንክ ስራ አስፈፃሚዎች ጋር ተወያይተዋል።

በውይይታቸውም በባንኮች ትብብርና በከተማ አስተዳደሩ ድጋፍ ስለሚገነባው ዘመናዊ የመኪና ማቆሚያና የንግድ ማዕከልን አንድ ላይ ያጣመረ የተቀናጀ ማዕከል ለመገንባት እየተከናወኑ ስላሉ ዝግጅቶች መክረዋል።

በተያያዘም የገቢ ግብርን ጨምሮ በንግድ ባንክ ብቻ ይሰጥ የነበረው እና በከተማ አስተዳደሩ ስር የሚሰበሰቡ ማንኛውንም የክፍያ አሰራር አገልግሎት በሁሉም የፋይናንስ ተቋማት ማድረግ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ እየተደረጉ ያሉ ጥናቶችና የደረሱበትን ደረጃ በተመለከተም ተወያይተዋል።

የተቀናጀ ማዕከሉ ግንባታው ሲጠናቀቅ ለወጣቶች የስራ እድል እንደሚፈጥር ከከንቲባ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.