Fana: At a Speed of Life!

በመዲናዋ የሚገኙ 24 የህዝብ የመዝናኛ ፓርኮች ለህዝብ ክፍት ሊሆኑ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥር 13፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ 24 የህዝብ የመዝናኛ ፓርኮች ለህዝብ ክፍት ሊሆኑ ነው።

ምክትል ከንቲባ ኢንጅነር ታከለ ኡማ ለአገልግሎት ክፍት የተደረገውን የፈረንሳይ ፓረክ ጎብኝተዋል፡፡

በከተማዋ የሚገኙ የህዝብ የመዝናኛ ፓርኮች ለአገልግሎት በሚመችና መሰረተልማት ባሟላ መልኩ እድሳት እየተደረገላቸው ሲሆን ጎን ለጎንም ለአገልግሎት ክፍት እንዲሆኑ ተወስኗል፡፡

ማንኛውም የከተማዋ ነዋሪም እነዚህን መዝናኛ ፓርኮች ያለክፍያ መጠቀም እንደሚችልም ነው የተጠቆመው፡፡

በጉብኝታቸው ወቅትም 1 ነጥብ 2 ኪሎ ሜትር የሚረዝመውና 15 ሜትር የጎን ስፋት የሚኖረው ከፈረንሳይ ፓርክ እስከ ፈረንሳይ አቦ ድረስ ያለው የመንገድ ግንባታ በአንድ አመት ውስጥ ይጠናቀቃል ብለዋል።

የነባር መንገዱ ችግር ለረጅም ጊዜያት የነዋሪዎቹ ጥያቄ ሆኖ የቆየ ሲሆን የነዋሪዎች እንቅስቃሴ ላይም ከፍተኛ ችግር ሲፈጥር ቆይቷል ነው የተባለው።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.