Fana: At a Speed of Life!

በመዲናዋ የማህበረሰቡን ችግር የሚፈታ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ምክር ቤት ሊቋቋም ነው

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 27፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ የበጎ ፈቃድ ተግባራት የማህበረሰቡን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግር የሚፈታ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ምክር ቤት ሊቋቋም ነው።

የከተማ አስተዳደሩ ህብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ቢሮ ምክትል ኮሚሽነር ሙሰማ ጀማል ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለጹት÷ በቀጣይ ለሚቋቋመው ምክር ቤት መመሪያ ጸድቆ ወደ ስራ ተገብቷል ብለዋል።

በበጋ ወራት ሲተገበሩ ከቆዩት ስራዎች በተጨማሪ በዘንድሮ ክረምት ወራት ከ3 ሺህ በላይ ቤቶች እንደሚታደሱ ነው የገለጹት፡፡

በተጨማሪም የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር፣ ማዕድ ማጋራት፣ የትራፊክ ማኔጅመንት ስራዎች፣በጎነት በሆስፒታል፣ደም ልገሳ እና ሌሎችም ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑን አብራርተዋል፡፡

የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ስራውን በተጠናከረ መልኩ ለማስቀጠልም ሁሉም  ዜጋ የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

በአፈወርቅ አለሙ

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

 

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.