Fana: At a Speed of Life!

በመዲናዋ የከባድ ተሽከርካሪዎች እንቅስቃሴ ሰዓት ማሻሻያ ተደረገበት

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 19 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ የከባድ ተሽከርካሪዎች እንቅስቃሴ ሰዓት ላይ ማሻሻያ ተደረገ።

በዚህ መሰረት ጠዋት ከ3 ጀምሮ እስከ ቀኑ 10 ሰዓት ከ30 ድረስ መንቀሳቀስ ይችላሉ ተብሏል።

ከዚህ ባለፈም ምሽት ላይ ከ12 ሰዓት በኋላ እንዲንቀሳቀሱ ተወስኗል።

ከዚህ ውጭ ግን ከባድ ተሽከርካሪዎቹ ከጠዋቱ 1 እስከ 3 ሰዓት ድረስ እንዲሁም ከሰዓት በኋላ ከ10 ከ30 እስከ ምሽት 12 ሰዓት ድረስ መንቀሳቀስ አይችሉም ነው የተባለው።

ማሻሻያው የተለያዩ ተቋማት በሰዓት ገደቡ ምክንያት በተለይም የግንባታ ስራዎች ለማከናወን ተቸግረናል የሚል ቅሬታ ማቅረባቸውን ተከትሎ መደረጉን ከከንቲባ ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

በመሆኑም የትራፊክ እንቅስቃሴውን ጫና ውስጥ በማይከት መልኩ ማሻሻያው ተደርጓል።

እስካሁን በነበረው ህግ በከተማዋ የሚገኙ ከባድ ተሽከርካሪዎች ከጠዋቱ 4 ሰዓት እስከ ቀኑ 10 ሰዓት ድረስ ብቻ ነበር መንቀሳቀስ የሚፈቀድላቸው።

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.