Fana: At a Speed of Life!

በመዲናዋ የዳቦ ዋጋ በሚጨምሩ እና ግራም በሚቀንሱ ተቋማት ላይ ህጋዊ እርምጃ እንደሚወሰድ ተገለፀ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 23 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ)በአዲስ አበባ ከተማ የዳቦ ዋጋ በሚጨምሩ እና ግራም በሚቀንሱ ተቋማት ላይ ህጋዊ አርምጃ እንደሚወሰድ የከተማዋ ንግድ ቢሮ አስታወቀ።

የአዲስ አበባ ከተማ ንግድ ቢሮ ባወጣው መግለጫ ከሰሞኑ አንዳንድ ዳቦ ቤቶች ያለ ምንም ምክንያት የዳቦ ዋጋ የመጨመር እና ግራም የመቀነስ ሁኔታ እየታየ መሆኑን ለማወቅ አንደተቻለ ነው የገለፀው።

ሆኖም ምንም አይነት የአቅርቦት ችግር በሌለበት በአሁኑ ወቅት በዚህ ድርጊት ውስጥ መሳተፍ በህግ የሚያስጠይቅ አንደሆነ ቢሮው ገልጿል።

ቢሮ በሚያደርገው ክትትል እና ጥቆማ መሰረት ከዚህ በኃላ በድርጊቱ ውስጥ በሚገኙ ዳቦ ቤቶች ላይ ህጋዊ እርምጃ እንዲወስድ አሳስቧል።

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.