Fana: At a Speed of Life!

በመዲናዋ ያለ ደረሰኝ ሽያጭ ሲያከናውኑ የነበሩ ከ22 በላይ ድርጅቶች ተያዙ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 18፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ ያለ ደረሰኝ ሽያጭ ሲያከናውኑ የነበሩ ከ22 በላይ ድርጅቶች መያዙን የከተማ አስተዳደሩ ገቢዎች ቢሮ አስታወቀ።
የአዲስ አበባ ከተማ ገቢዎች ቢሮ ባደረገው ድንገተኛ ክትትል ድርጅቶቹን በህግ ቁጥጥር ስር ማዋል መቻሉን አስታውቋል።
የቢሮው ኃላፊ አቶ ሙሉጌታ ተፈራ እንደገለጹት፥ በከተማዋ የተለያዩ የንግድ ድርጅቶች ላይ በተደረገ የክትትል ቁጥጥር ስራ ድርጅቶቹ ተይዘዋል።
በተጨማሪም በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 6 ቄራ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ የፖሊስ ልብስ በመልበስና ሃሰተኛ የገቢዎች ቢሮ መታወቂያ በማሰራት ግብር ከፋዩን ህብረተሰብ ሲያጭበረብሩ የነበሩ ሁለት ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ውለዋል ብለዋል።
በቁጥጥር ስር በዋሉ ግለሰቦች ላይም በፖሊስ ምርመራ እየተደረገባቸው መሆኑን አቶ ሙሉጌታ ተፈራ መናገራቸውን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፕሬስ ሴክሬታሪያት መረጃ ያመለክታል።
በከተማዋ የግብር ህግን አክብረው በማይሰሩ ነጋዴዎች ላይ ህግን የማስከበር ስራ እየተከናወነ መሆኑን የገለጹት ኃላፊው ግብር ከፉዩ የወጣውን የግብር ህግ አክብሮ እንዲሰራ ጥሪ አቅርበዋል።
ህብረተሰቡም የወጣውን የግብር ህግ አክብረው የማይሰሩ አጭበርባሪዎችን በሚመለከትበት ወቅት 7075 ነጻ የስልክ መስመር በመጠቀም ጥቆማ እንዲሰጥም ጠይቀዋል።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.