Fana: At a Speed of Life!

በመዲናዋ ጥንቃቄ ሳይደረግ የሚካሄዱ ግንባታዎች በመንገድ መሰረተ ልማት ላይ ችግር እየፈጠሩ ነው

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 26 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ የተለያዩ አካባቢዎች ጥንቃቄ ሳይደረግ የሚካሄዱ ግንባታዎች በመንገድ መሰረተ ልማት ላይ ችግር እየፈጠሩ ነው።

በከተማዋ የተወሰኑ ግለሰቦች እና ድርጅቶች ግንባታ ሲያካሂዱ አሸዋ እና የግንባታ ቁሳቁሶችን ከህግ ውጭ መንገድ ዳር ሲያከማቹ ይስተዋላል።

ይህም የትራፊክ መጨናነቅን በመፍጠር መንገዱን ለእግረኞች አስቸጋሪ እንዳደረገው ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ተዘዋውሮ በተመለከታቸው አካባቢዎች መታዘብ ችሏል፡፡

ከዚህ ጋር ተያይዞም የመንገድ ብልሽት እንዲፈጠር በማድረግም ለጥገና ከፍተኛ ወጪ እያስወጣም ይገኛል ነው የተባለው፡፡

የአዲስ አበባ መንገዶች ባለስልጣን የመንገዶች ጥገና ዳይሬክተር ኢንጅነር መኮንን ጥበቡ በግንባታ ፍቃድ አሰጣጥ ላይ የሚስተዋለው ክፍተት ለችግሩ መንስኤ መሆኑን ይናገራሉ፡፡

የግንባታ ፍቃድ ሲሰጥ በተወሰነ ደረጃ የግንባታ ደረጃዎችን ሳያገናዝብ የሚሰጥ እንዳለ መረዳት ችለናልም ነው ያሉት።

ዳይሬክተሩ በህዝብ ገንዘብ የሚሰሩ መሰረተ ልማቶች በእንዲህ መሰል ህገ ወጥ ድርጊት ለውድመት እንዳይጋለጡ የግንባታ ፍቃድ ከሚሰጡ አካላት ጋር ያለውን ግንኙነት ይበልጥ ለማጠናከር እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡

በስላባት ማናዬ

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳ
የፋና ድረ ቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.